Select Page

ዳሸን ባንክ ከኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ እና ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር ያቀረበው “ጌትፊ ፔይ ባይ ሊንክ” (GetFee – Pay By Link) የተሰኘ የኦንላየን የክፍያ አማራጭ አገልግሎት አስተዋወቀ፡፡

ዳሸን ባንክ ከኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ እና ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር ያቀረበው “ጌትፊ ፔይ ባይ ሊንክ” (GetFee – Pay By Link) የተሰኘ የኦንላየን የክፍያ አማራጭ አገልግሎት አስተዋወቀ፡፡

አዲሱ የክፍያ አገልግሎት አማራጭ ተጠቃሚዎች ለገዙት ወይም ላገኙት አገልግሎት በማስተር፣ በቪዛ እና አሜሪካን ኤክስፕረስ ካርዶችን በመጠቀም በኦንላየን ክፍያ መፈጸም የሚችሉበት አሰራር ነው፡፡

የዳሸን ባንክ ቺፍ ዲጂታልና ኢንፎርሜሽን ኦፊሰር የሆኑት አቶ ዮሐንስ ሚሊዮን አገልግሎቱ የንግድ ተቋማት ያለ ሶስተኛ ወገን ተሳትፎ ግብይት እንዲፈጽሙ እንደሚያስችል ጠቁመው ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ የክፍያ አማራጭ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

አገልግሎቱ ደንበኞች ከተገለገሉበት ወይም ግዢ ከፈጸሙበት ድርጅት የክፍያ መጠየቂያ የያዘ ሊንክ በኢሜል ወይም በዋትስአፕ እንዲደርሳቸው የሚያደርግ ሲሆን በመቀጠልም የተላከላቸውን ሊንክ (ማስፈንጠሪያ) በመጫን ወደ ክፍያ ገጽ እንዲገቡ የሚስችል ነው፡፡

ሆቴሎችና ሌሎች የንግድ ተቋማት ምንም አይነት የቴክኖሎጂ ግዥ መፈጸም ሳይጠበቅባቸውና ከኮሚሽን ክፍያ ነጻ በሆነ አሰራር ፖርታል ላይ የንግድ ሂደታቸውን ለማሳለጥ እንደሚያግዛቸው ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም የንግድ ተቋማቱ የሚያቀርቡትን ምርትና አገልግሎት ወደ ማሕበራዊ ሚዲያ አማራጮች በማምጣት ስራቸውን በሚፈልጉት መንገድ ማስተዋወቅ የሚያስችል ነው።

የኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በርሱፈቃድ ጌታቸው በበኩላቸው አገልግሎቱ የጥሬ ገንዘብ ዝውውርን በመቀነስ የክፍያ ሂደቶችን የተሳለጠ እንደሚያደርግ አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም ለድርጅቶች የውጭ ምንዛሬ በቀጥታ በማስገኘት ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

Other Photo Albums

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram