Select Page

ዳሸን ባንክ ከኤግል ላየን ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ከወለድ-ነጻ የዱቤ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል “ከወለድ-ነጻ ዱቤ አለ” አገልግሎትን አስተዋወቀ፡፡

ከወለድ-ነጻ ዱቤ አለ “IFB DubeAle” የሸሪዐህ መርሆዎችን ተከትሎ የሚሰራ አገልግሎት ሲሆን እንደ ሽያጭ ውል የሚሰራና በደንበኛው ጥያቄ መሰረት የዱቤ አገልግሎት የሚያገኝበት አሰራር ነው ፡፡

ስለ አገልግሎቱ ማብራሪያ የሰጡት የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይና ቺፍ ባንኪንግ ኦፕሬሽን ኦፊሰር አቶ ጥበቡ ሰለሞን በባንኩ ከወለድ-ነጻ ሂሳብ ያለው ደንበኛ አገልግሎቱን መጠቀም እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

ባንኩ አዳዲስ አገልግሎቶችን የማስተዋወቅ ጥረቱን በመቀጠል አሁንም ከኤግል ላየን ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር የቆየውን የማህበረሰባችንን የዱቤ ግብይት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና አስተማማኝ የባንክ አሰራር በማገዝ “ከወለድ-ነጻ ዱቤ አለ” የተሰኘና ሸማቾች በዱቤ በፈለጉት ጊዜ ያሻቸውን ገዝተው ቆይተው ከወለድ-ነጻ በሆነ መንገድ መክፈል የሚችሉበትን አሰራር እንዳስተዋወቀም ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ደምበኛው ቋሚ ንብረት ካለው እንደ ዋስትና ማስያዥያ አልያም የሶስተኛ ወገን ዋስትና ማቅረብ ይችላል። ደምበኛው በባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ካለው ጥሬ ገንዘብ (በዉጭ ምንዛሬ ወይም በብር) ዋስትና ማስያዝ እንደሚችልም ተብራርቷል።

ዳሸን ባንክ አሁን ላይ ባስተዋወቀው “ከወለድ ነጻ-ዱቤ አለ አገልግሎት” ደንበኞች እስከ 700,000.00 (ሰባት መቶ ሺህ ብር) ድረስ ያሻቸውን መሸመት ያስችላቸዋል፡፡

ከወለድ ነጻ ዱቤ አለ ተጠቃሚዎች ዛሬ ለገዙት በሸሪዓህ ህግ የተፈቀዱ ምርትና አገልግሎቶች ክፍያውን ወደፊት የሚከፍሉ ሲሆን አከፋፈሉም እንደ ደንበኛው ምርጫ በ3 ወር፣በ6 ወር እና በ12 ወር ይሆናል፡፡

Other Photo Albums

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram