Select Page

ዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ከኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ከወለድ ነጻ ዱቤ አለ አገልግሎት በሐረር አስተዋወቀ።

ዳሸን ባንክ እያስተዋወቃቸው የሚገኙ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች የንግድ ስርዓቱን ለማዘመን አጋዥ ናቸው ተባለ

ዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ከኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ከወለድ ነጻ ዱቤ አለ አገልግሎት በሐረር አስተዋወቀ።

አገልግሎቱን አስመልክቶ ከከተማው የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎች የታደሙበት የግንዛቤ መፍጠሪያ መርሐ-ግብር ተዘጋጅቷል።

መርሐ-ግብሩን በንግግር የከፈቱት የዳሸን ባንክ ቺፍ ስትራቴጂክ ኦፊሰር  አቶ ኤልያስ ሁሴን የዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት (ሸሪክ) ቀላልና ቀልጣፋ ዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን ለማጠናከር እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የሐረሪ ክልል የንግድና ቁጥጥር ዳይሬክተር ሚሊዮን ጽጌ በበኩላቸው  የንግድ ስርአቱን የተሻለ ለማድረግ ዳሸን ባንክ እንደ ሀገር  እያበረከተ ያለው  አስተዋጽኦ የሚበረታታ እንደሆነ ተናግረዋል።

የዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ እና ኤጀንሲ ባንኪንግ ዳይሬክተር አቶ አምዱ ሰማን እንዲሁም የኤግል ላይንስ ሲስተምስ ቴክኖሎጂ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ዳዊት አለማየሁ  አገልግሎቱን አስመልክቶ ዝርዝር ማብራሪያ አቅርበዋል።

በሴሚናሩ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ ከታዳሚዎች ለተነሱ ጥያቄዎች የባንኩ ከወለድ ነጻ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ መስፍን በዙ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

 

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram