Select Page

ዳሸን ባንክ ካልቸር ክለብ 11ኛውን የቦርሳ ዐውደ-ርዕይ አዘጋጀ

ዳሸን ባንክ ካልቸር ክለብ 11ኛውን የቦርሳ ዐውደ-ርዕይ (The Bag Show) ባሳለፍነው አርብ በሸራተን አዲስ ሆቴል አከናውኗል፡፡

የሀገር በቀል ዲዛይነሮችን የፈጠራ ውጤቶች ለማስተዋወቅና ለማበረታታት በዳሸን ባንክ ካልቸር ክለብ በየዓመቱ የሚዘጋጀው የቦርሳ ዐውደ-ርዕይ ለ11ኛ ጊዜ በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል።

የአውደ-ርዕዩ ተሳታፊዎች የመግቢያ ትኬት ክፍያቸውን በዳሸን ሱፐር አፕ በኩል ፈፅመዋል፡፡

ዐውደ-ርዕዩ በኢትዮጵያውያን ዲዛይነሮች የሚሰሩ የእጅ ቦርሳዎችንና የጥበብ ስራዎችን ለታዳሚው በማቅረብ ረገድ ትልቅ ስም ያተረፈ ሲሆን፤ በዘንድሮው መርሃ-ግብር ላይም ከ18 በላይ የአገር ውስጥ ዲዛይነሮች የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለዕይታ አቅርበዋል።

የዘንድሮው የቦርሳ ዐውደ-ርዕይ የጥበብ ስራዎችን ከማሳየት ባለፈ ማኅበራዊ ኃላፊነትን ያነገበ ሆኖ አልፏል።

በዕለቱ ከእያንዳዱ ቦርሳ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ 20 በመቶ እንዲሁም ከጨረታ የሚገኘው ገቢ ሙሉ ለሙሉ ‘ፋዘር ኪችን’ ለተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ድጋፍ እንደሚውል ተገልጿል።

ዳሸን ባንክ እየሰጣቸው ከሚገኙ ዘመናዊና ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎቶች ባሻገር ባሕልና ጥበብን ለማበረታታት በዳሸን ባንክ ካልቸር ክለብ  አማካኝነት የተለያዩ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል።

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram