ዳሸን ባንክ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን አከበረ
22ተኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በስነ ምግባር፤ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ሐሳብ በዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ተከበረ።
የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይና በዳሸን ባንክ ቺፍ ስትራቴጅክ ኦፊሰር አቶ አየለ ተሾመ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሙስና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል እንደመሆኑ ሀገራትና ተቋማት ወንጀሉን ለመዋጋት ትብብር እያደረጉ መሆኑን አንስተዋል።
ዳሸን ባንክ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት 22ተኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን እያከበረ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ አየለ፣ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል እንዲሁም የባንኩ አሰራር ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በባንኩ የኢቲክስና ኮንዳክት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ጥላዬ እንየው ዳሸን ባንክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ተኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የፀረ-ሙስና ቀን በተለያዩ መርሃ-ግብሮች እያከበረው እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ባንካችን እያከበረበት የሚገኘው ዋና ዓላማ በባንካችን ሊከሰቱ የሚችሉ የሙስና ስጋትና ተጋላጭነቶችን ለመፈተሽና እንዲሁም በዘርፉ ያለውን ችግር በመረዳት የበኩላችንን ለመወጣት የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የፌደራል ስነምግባር እና የጸረ -ሙስና ኮሚሽን በዓሉን አስመልክቶ ያዘጋጀውን ሰነድ የበዓሉ ተሳታፊዎች እንዲከታተሉ ከተደረገ በኋላ በቀረበው ሰነድ ላይ በአቶ አየለ ተሾመ አማካኝነት የበዓሉ ተሳታፊዎች ውይይት አድርገዋል፡፡
በመርሃ-ግብሩ የባንኩ የስራ ኃላፊዎች የሐብት ምዝገባ ሰነድ ርክክብ ተከናውኗል።
