Select Page

ዳሸን ባንክ ዘመናዊ የዱቤ ግብይትን ባስተዋወቀበት የ”ዱቤ አለ” አገልግሎት ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ አበደረ

ዳሸን ባንክ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ምርትና አገልግሎት አቅራቢ የንግድ ድርጅቶች ጋር በጥምረት ባቀረበዉና ዘመናዊ የዱቤ ግብይትን ባስተዋወቀበት የ”ዱቤ አለ” አገልግሎት ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ አበደረ፡፡

ባንኩ ከጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ባስጀመረው በዚህ አገልግሎት ከ21,000 በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ማቅረብ የቻሉ ሲሆን፣ ከ470,000 ሺህ በላይ የሆኑ ደንበኞች ደግሞ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

“ዱቤ አለ” ዳሸን ባንክ ከኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ምርትና አገልግሎት የሚያቀርቡ የንግድ ድርጅቶች ጋር በጥምረት ያቀረበዉ በቴክኖሎጂ የታገዝ የዱቤ አሰራር ሲሆን፣ በመደበኛና የሸሪዐህ መርሆዎችን በተከተለ አሰራር በቀረበው በዚህ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችንና በርካታ አገልግሎቶችን በ3 ወር፣ በ6 ወርና በ12 ወር በሚመለስ ዱቤ በወለድና ያለወለድ መግዛት የሚያስችል አማራጭ ነው፡፡

 

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram