ዳሸን ባንክ የተሳተፈበት ኤክስፖ ተከፈተ
ዳሸን ባንክ የተሳተፈበት “አዲስ ነገር እሰከ ፋሲካ” ኤክስፖ በዛሬው ዕለት በኤግዚቢሽን ማዕከል በይፋ ተከፍቷል ።
በዚህ ኤክስፖ ላይ የተሳተፈው ዳሸን ባንክ በቅርቡ በባንክ ኢንዱስትሪው ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የሆነውን ዳሸን ባንክ ሱፐር አፕን ጨምሮ ዱቤ አለ እና ሌሎች መደበኛ የባንኩን አገልግሎቶች ያስተዋውቃል ።
ኤክስፖው ለቀጣይ 22 ቀናት እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን ዳሸን ባንክም ምሽትን ጨምሮ የባንክ አገልግሎት ለተሳታፊዎች ይሰጣል ።
እሰከ ፋሲካ ዋዜማ ድረስ በሚቆየው ይህ ኤክስፖ ሀገር በቀል ድርጅቶች እና ከተለያዩ ዓለም ሀገራት የመጡ አምራችና ነጋዴዎች የሚሳተፉበት ሲሆን እሰከ ሦስት መቶ ሺህ ድረስ የሚገመቱ ጎብኚዎች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል ።