Select Page

ዳሸን ባንክ የታላቁን ረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ “ለእናቴ” በሚል ስያሜ የሰደቃ መርሀ-ግብር እያከናወነ ይገኛል

የዳሽን ባንክ ባህር ዳር ዲስትሪክት የታላቁን የረመዳን ወር ጾምን ምክንያት በማድረግ “ለእናቴ” የተሰኘ የሰደቃ መርሀ ግብር አካሄደ፡፡

ዲስትሪክቱ በአማራ ክልል እስልምና ጉዳዩች ከፍተኛ ምክር ቤት አማካይነት መደገፍ አለባቸው ብሎ ለለያቸው 50 አቅመ ደካማ ሴቶች፣ ህጻናት እና አረጋውያን ድጋፍ አድርጓል፡፡

የዲስትሪክቱ የማኔጅመንት አባላት እና የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አጠቃላይ ወጪው 242, 000 ብር በላይ የሆነ የዱቄት፣ የዘይትና የቴምር ስጦታ ተበርክቷል።

በሰደቃ መርሀ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሸህ ሙሃመድ ኢብራሂም ዳሸን ባንክ ይህን መሰል ተግባር ሲፈጽም የመጀመሪያው አለመሆኑን ጠቅሰው፤ ባንኩ ላደረገው ድጋፍ በምክር ቤቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ ከባንኩ ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚያጠናክር መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ባህር ዳር ዲስትሪክት ቢዝነስ ዳይሬክተር ተወካይ የሻምበል በቃሉ በበኩላቸው ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እያከናወናቸው የሚገኙ ተግበራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ከክልሉ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ጋር ያለውን ግንኑነት በማሳደግ በትብብር እንደሚሰራም አስረድተዋል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው እናቶችም ባንኩ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ዳሸን ባንክ “ለእናቴ” በሚል ስያሜ የጀመረውን የሰደቃ መርሀ-ግብር በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ማከናወኑን ይቀጥላል፡፡

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram