Select Page

ዳሸን ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እያስተባበረው ባለው ኤግዚቢሽን በመሳተፍ ላይ ነው


ዳሸን ባንክ ከኅዳር 17-21/2018 በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ባለው ኤግዚብሽን በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

‎”የፋይናንስ እውቀትን ማጎልበት፣ የደንበኞችን የፋይናንስ ደህንነት ማጠናከር” በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስተባባሪነት እየተከናወነ ባለው በዚህ መርሃ-ግብር ዳሸን ባንክ ለባንክ ኢንዱስትሪው የመጀመሪያ የሆነውን ሱፐር አፕን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ አገልግሎቶቹን ለጎብኚዎች በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።

‎በኤግዚቪሽኑም ደህንንቱ የተጠበቀ የደንበኞች የፋይናንስ ትምህርት አገልግሎት ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል።

በክልሉ የባንክ አገልግሎት ተደራሽ ባልሆኑ አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግና የዜጎችን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እውቀትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከመንግስትና ከግል ባንኮች ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑ
‎ተገልጿል።

መሰል መርሃ-ግብር በሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ) እንዲሁም በአፋር ክልል (ሰመራ) እየተከናወነ ሲሆን ዳሸን ባንክም የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛል።

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram