ዳሸን ባንክ 18 ቢሊዮን ብር ገቢ አስመዘገበ
ዳሽን ባንክ 18 ቢሊዮን ብር ገቢ አስመዘገበ
ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት አመት ብር 18 ቢሊዮን ገቢ አስመዘገበ፡፡ የባንኩ ባለአክስዮኖች 30ኛ መደበኛ ጉባኤ በስካይላይት ሆቴል ዛሬ የተካሔደ ሲሆን ያለፈው አመት የባንኩ የስራ አፈጻጸም ፣ የዚህ በጀት አመት እቅድና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ውይይት ተደርጎባችዋል፡፡
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የዳሸን ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን ያለፈው በጀት አመት በባንክ ኢንዱስትሪው አዎንታዊና አሉታዊ ሁኔታዎቸን የፈጠሩ አለም አቀፋዊና አገራዊ ክስተቶች እንደነበሩ አስታውቀዋል፡፡
አቶ ዱላ ባለፈው በጀት አመት በኢትዮጵያ የነበረው ማህበራዊና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንዲሁም ኢሚዛናዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ በባንክ ኢንዱስትሪው ላይ የበኩሉን ተጽእኖ ማሳደሩን አስገንዝበዋል፡፡
ምንም እንኳን የተለያዩ ተግዳሮቶች የነበሩበት አመት ቢሆንም ዳሸን ባንክ ባለፋ በጀት አመት በበርካታ ዘርፎች ውጤታማ እንደነበር አቶ ዱላ ገልጸዋል፡፡ ባንኩ ተጨማሪ 23.6 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ የቻለ ሲሆን አጠቃላይ ሀብቱን 144.6 ቢሊዮን ብር ማድረስ ተችሏል፡፡
ባንኩ በአመቱ የ18 ቢሊዮን ብር ገቢ አስመዝግቧል፡፡ ከትርፍ አኳያ ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት አመት ከግብር በፊት 5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ያገኘ ሲሆን ይህም ከቀደመው አመት ጋር ሲነጻጸር የ31.9 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡
የባንኩ የአምስት አመት ስትራቴጅክ እቅድ የትግበራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎም በቀጣይ አምስት አመታት ተግባራዊ የሚሆን አዲስ ስትራቴጅክ እቅድ መዘጋጀቱን ይህ እቅድ የደንበኞች አገልግሎት በማሻሻል ፣ አገልግሎትን ይበልጥ በማዘመንና የባንኩን ቀጣይ እድገት ላይ እንደሚያተኩር አመልክተዋል፡፡
Other Photo Albums

ዳሸን ባንክ 6.4 ቢሊየን ብር ትርፍ አስመዘገበ

ዳሸን ባንክ የ6ኛውን የታማኝ የግብር ከፋዮች ሽልማት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ

Dashen Bank Culture Club 2017 EC Events Calendar Unveiled!

Dashen Bank Participates in NBE’s Launch of DEBO Initiative to Boost Remittances

ዳሸን ባንክ ከኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ እና ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር ያቀረበው “ጌትፊ ፔይ ባይ ሊንክ” (GetFee – Pay By Link) የተሰኘ የኦንላየን የክፍያ አማራጭ አገልግሎት አስተዋወቀ፡፡

ዳሸን ባንክ ከኤግል ላየን ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ከወለድ-ነጻ የዱቤ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል “ከወለድ-ነጻ ዱቤ አለ” አገልግሎትን አስተዋወቀ፡፡

የዳሸን ባንክ 28ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እና የሠራተኞች ቀን

ሶስቱ ጓደኛማቾች የዳሸን ከፍታ ውድድርን አሸነፉ!

ዳሸን የ“ዘ ባንከር” ሽልማትን ለ13ኛ ጊዜ አሸነፈ

ዳሸን ባንክ የአለም አቀፉ አነስተኛና መካከለኛ ተቋማት ፋይናንስ ፎረም አባል ሆነ

ዳሸን ባንክ፣ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደርና የከተማው የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ

ዳሸን ባንክ የ2015 የባንኮች የእግር ኳስ ውድድር ዋንጫ አሸነፈ

ዳሸን ባንክና ማስተርካርድ የመጀመሪያውን ቨርቹዋል አለም አቀፍ ቅድመ ክፍያ ካርድ አስተዋወቁ::

ዳሸን ባንክ በቴክኖሎጂ የታገዘ የዱቤ ግብይት አስተዋወቀ

Donation to Somali Regional State

Dashen American Express International card Inaguration

28th Ordinary & 25th Extra Ordinary Annual Shareholder Meeting at Mechare Meda

The 27th Ordinary and 24th Extra Ordinary General Meeting of Shareholders of Dashen Bank

ዳሽን ባንክ የ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ መከላከያ ዝግጅት አበረከተ
