ገራድዊልዋል ከወለድ ነጻ ቅርንጫፍ በይፋ ተመረቀ

ገራድዊልዋል ከወለድ ነጻ ቅርንጫፍ በይፋ ተመረቀ
ዳሸን ባንክ ጅግጅጋ ከተማ የሚገኘውን ገራድዊልዋል ከወለድ ነጻ ቅርንጫፍ በይፋ አስመረቀ።
የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድወሰን አብርሃም ደንበኞች ዘወትር የዳሸን አጋር በመሆናቸው አመስግነዋል ። በቀጣይም አብረን እንሰራለን ብለዋል።
የዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ መስፍን በዙ የባንኩን ደንበኞች አመስግነዋል።
ጅግጅጋ ላይ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የጀመረው ከአራት ዓመት በፊት በገራድዊልዋል ቅርንጫፍ መሆኑን የጠቀሱት አቶ መስፍን ቅርንጫፉ እንዲከፈትና በአጭር ጊዜ ወደ ስራ እንዲገባ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
“ተጋግዘን ጠንካራ ስራዎችን እንሰራለን” ያሉት አቶ መስፍን የክልሉን የልማት ስራዎች ለመደገፍ ዳሸን ባንክ ከጎናችሁ ይቆማል ብለዋል ።
በምረቀ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙ የባንኩ ደንበኞች በበኩላቸው የዳሸን ባንክ ልኡካንን እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል። ዳሸን ባንክ ሴቶችን በማበርታት እያበረከተ ስላለው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅረበዋል ።
ባንኩ ከወለድ ነጻ በሆነ የባንክ አገልግሎት አካታችና ጠንካራ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ በመሆኑ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
ዜጎች ሕይወታቸውን እንዲቀይሩ በቀጣይም ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበትም ገልጸዋል።


