Select Page

ለዳሸን ባንክ አ.ማ ባለአክስዮኖች በሙሉ

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ የዕጩ አባላትን ጥቆማ ከመጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየተቀበለ መሆኑ ይታውቃል። ስለሆነም ለባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት መስፈርቱን የሚያሟሉ ዕጩዎችን እስከ ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጠቆም የምትችሉ ሲሆን ስለተጠቋሚዎች መስፈርት እና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች ከባንኩ ድረ-ገፅ www.dashenbanksc.com እንዲሁም መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከወጡት ሪፖርተር አማርኛው እና አዲስ ዘመን ጋዜጦች ማግኘት የሚቻል መሆኑን እየገለፀ፤ የጥቆማ ማቅረቢያ ቅፁን ከሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች፤ ከባንኩ ዋና መ/ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጊዜያዊ ጽ/ቤት እና ከባንኩ ድረ ገፅ ማግኘት የሚቻል መሆኑን በአክብሮት ያሳውቃል፡፡

ማሳሰቢያ፡ የጥቆማ መስጫ ወረቀቱ በፖስታ ታሽጎ በአቅራቢያ ላሉ የባንኩ ቅርንጫፎች ወይም ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 14ተኛ ፎቅ ላይ ለሚገኘው የአስመራጭ ኮሚቴው ጊዜያዊ ፅ/ቤት ሊመለስ የሚገባ ሲሆን ከሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም በኋላ ጥቆማ ለማቅረብ የሚቀርብ ጥያቄም ሆነ ከዚህ ጊዜ በኋላ ባንኩ ጋር የሚደርስ የጥቆማ መስጫ ወረቀት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በአክብሮት ያሳውቃል፡፡

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram