Select Page

ዳሸን ባንክ እና ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከአዲስ አበባ መስተዳደር ጋር በመተባበር በልደታ ክ/ከተማ ያስገነቡትን ሁለተኛውን የምገባ ማዕከል ዛሬ ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም በይፋ አስመረቁ።

የምገባ ማዕከሉ በከተማዋ ውስጥ ላሉና በቀን አንድ ጊዜ እንኳን መመገብ ለማይችሉ ወደ 3 ሺህ ለሚጠጉ ዜጎች ጤናውን የጠበቀ ምግብ እንዲያገኙ የሚያግዝ ሲሆን ከዚህ ቀደም በከተማው አስተዳደር ውስጥ ከሚገኙት ጋር ተጨምሮ በጠቅላላው ሰባተኛው የምገባ ማዕከል ይሆናል፡፡

አጠቃላይ የግንባታ ወጪው 40 ሚሊዮን የተገመተው ይህ የምገባ ማዕከል ሙሉ ወጪውን ዳሸን ባንክ ከሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በመተባበር የሸፈኑት ሲሆን፣ የአንድ ዓመት የምገባ ወጪውንም (21 ሚሊየን ብር) ሁለቱ ድርጅቶች በጣምራ የሚሸፍኑት ይሆናል፡፡

በሀገራችን ብሎም በመዲናዋ አዲስ አበባ እየተንሰራፋ የመጣውን ድህነት ከመቅረፍ አንፃር የምገባ ማዕከሉ ትልቅ አስተዋጽዖ ይኖረዋል።

ዳሸን ባንክና ሚደሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር ባደረት ስምምነት ተስፋ ብርሃን አሙዲ ቁጥር 1 የምገባ ማዕከል አቋቁመው በየዕለቱ ሁለት ሺህ ለሚሆኑ በቀን አንድ ጊዜ ምሳ በማቅረብ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ።

በፕሮጀክቱ የምገባ አዳራሽ፣ የተፈናቀሉ ሠዎች የቀድሞ ሕይወታቸው እንዲቀጥል 23 ሱቆች፣

ለተፈናቀሉ ወገኖች 8 የመኖሪያ፣ እንዲሁም ለምገባ አገልግሎቱ የሚውል የጓሮ አትክልት ግንባታ ተከናውኗል።

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram