Select Page

ዳሸን ባንክ ከኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

 (ሚያዚያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም/አዲስ አበባ) ዳሸን ባንክ እና ኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ዱቤ ፔይ ቴክኖሎጂ በተሰኘ መተግበሪያ አማካኝነት ለደንበኞቻቸው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

መተግበሪያው የንግድ ተቋማት ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ለሸማቾች ለዱቤ ማቅረብ የሚያስችላቸውን ይኸም ­ሽያጫቸውን ለማሳደግ እንደሚረዳ ተጠቅሷል፡፡ ሸማቾችም ጊዜያዊ የገንዘብ እጥረታ ወቅታዊ ፍላጎታቸውን ከማሳካት እንዳያግዳቸው እና ያሉባቸውን ክፍያዎች በቴክኖሎጂ በመታገዝ በተራዘመ ጊዜ ለመፈፀም ያስችላቸዋል፡፡ 

በፊርማ ስነ-ሥርዓቱ ወቅት እንደተገለጸው ዱቤ ፔይ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሟላና ደህንነቱ አስተማማኝ ዘመናዊ መተግበሪያ ነው። ኤግልላይን ሲስተም ቴክኖሎጂ በተለይዩ ዘርፎች የተሰማራ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን፣ ካሽ ጎ፣ ጉዞ ጎና  ጌት ሩምስን ጨምሮ በርካታ መተግበሪያችን አበልጽጓል።

ዳሸን ባንክ የኤሌክትሮኒክ ክፍያ ካርድ በማስተዋወቅ ረገድ ፈር ቀዳጅ ሲሆን፣ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ከሞኔታ ቴክኖሎጂ አ.ማ ጋር በመተባበር አሞሌ የተሰኘውን ዘመናዊ የክፍያ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በቀጣይም ባንኩ በተናጥል እንዲሁም ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር ይፋ የሚያደርጋቸው ፕሮጀክቶች እንዳሉ ተጠቁሟል።

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram