Select Page

ፍለተርዌቭ ገንዘብ የማስተላልፍ አገልግሎትን ለማመቻቸት ከዳሸን ባንክና ከሞኔታ ቴክኖሎጂስ ጋር አጋርነትን መሰረተ

ፍለተርዌቭ ገንዘብ የማስተላልፍ አገልግሎትን ለማመቻቸት ከዳሸን ባንክና ከሞኔታ ቴክኖሎጂስ  ጋር አጋርነትን መሰረተ

አዲስ አበባ፡ ግንቦት 12 2013 – በአፍሪካ የክፍያ ቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን እየመራ የሚገኘው ፍለተርዌቭ ዛሬ በኢትዮጵያ ታላቁ ከሆነው የዲጂታል ዋሌት መገልገያ አሞሌ ጋር አጋርነት መመስረቱን አስታውቋል። ይህም አሞሌን በመጠቀም በአሞሌ ዋሌት፣ በባንክ ሂሳቦች እንዲሁም ከ2500 በላይ ባሉ የገንዘብ ማውጫ ቦታዎች ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ እንዲተላለፍ ያስችላል።

አሞሌ ተጠቃሚዎቹ ዲጂታል እቃዎችንና አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙና በቀላሉ ዋና ዋና ክፍያዎችን ባሉበት ሆነው እንዲፈፅሙ ያመቻቻል። ከፍለተርዌቭ ጋር የተመሰረተው አጋርነት በአመት ወደ ኢትዮጵያ ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለሚልኩ ከ8 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች የገንዘብ ማስተላለፍ ሒደቱን በማቅለል የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ይደግፋል። አለማቀፍ ገንዘብ አስተላላፊዎች፣ ፍለተርዌቭን የሚጠቀሙ የንግድ ተቋማት እንዲሁም የፍለተርዌቭ ባርተር አገልግሎት ተጠቃሚዎች በዚህ አጋርነት ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ መላክ ይችላሉ።

አሁን በኢትዮጵያ ያለው የገንዘብ ማስተላለፍ ሒደት ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ውድ ከመሆኑ በተጨማሪ አሰልቺ የወረቀት ስራውን እና የሚከሰቱ መዘግየቶችትን ተከትሎ አስቸጋሪ እና ብዙ ጊዜ የሚወስድ ሆኖባቸዋል። ይሄ አጋርነት ያለምንም ክፍያ ወዲያውኑ ገንዘብን በፈለጉበት ቦታ እና ጊዜ መቆጣጠር ወይም ማየት በሚችሉበት መልኩ ማስተላለፍ እንዲችሉ በማድረግ ይህንን ችግር ይቀርፋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ  ሪፖርት መሰረት ከ75% በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የባንክ አገልግሎቶችን የማይጠቀም ሲሆን ወደ 40% የሚጠጉ የባንክ ቅርንጫፎች በሙሉ የሚገኙት በመዲናዋ አዲስ አበባ ነው። በሦስቱ ተቋማት መካከል የተፈጠረው ትስስር ለኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች የገንዘብ ማስተላለፍ ሂደቱን በማመቻቸት በ75 ፐርሰንቱ የሚመሩ አነስተኛ እና እያደጉ ላሉ ንግዶች እድሎችን በመስጠት መዳረሻውን ላላገኙ ለነዚህ የህበረተሰቡ ክፍል ጠቃሚ አገልግሎትን ይሰጣል። ተጠቃሚዎች ፈቃድ ካላቸው 2500 የአሞሌ ወኪሎች ገንዘብ መውሰድ ስለሚችሉ በሀገሪቷ በተለያየ የኢኮኖሚ ደረጃ ያሉ ሰዎች ተሳትፎ ይጨምራል።

የፍለተርዌቭ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ኦለግቤንጋ አግቡላ ስለአጋርነቱ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል። “ዲጂታል የሆነ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎትን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ከዳሸን ባንክና ሞኔታ ቴክኖሎጂስ ጋር በመስራታችን በጣም ደስተኞች ነን። በሀገሪቱም ሆነ በአህጉሩ ያለውን የተለያዩ የኢኮኖሚ ደረጃዎች ተሳትፎ ክፍተት ለማጥብበ በምናደርገው ጉዞ ይሄ ወሳኝ ምእራፍ ነው። በጣም የምንተጋለት አንዱ ግባችን በኢትዮጵያ ያሉ የንግድ ተቋማት ከመላው ዓለም እንዲከፈሉ በማስቻል ንግዳቸውን የሚያሳድግ ትልልቅ የእድል በሮችን መክፈት ነው። ትብብሩ ይህንን አላማ አመርቂ በሆነ መልኩ ያሳካልናል። ይህ ገና ጅማሬው ነው። አጋርነታችንን ከዚህ በበለጠ በማጥበቅ በሁሉም ቦታ ያሉ አፍሪካውያን ለመጥቀም ተስፋ አለን።”

የዳሽን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው አለሙ  “ደንበኞቻችንንም ሆነ ሀገራችንን የሚደግፍ ወሳኝ የሆነ የውጭ ምንዛሬ ገበያን ከፍለተርዌቭ ጋር ተሻርከን በማቅረባችን ደስተኞች ነን። ይሄ ትስስር በቅርቡ ዓለም አቀፍ ኢ-ኮሜርስን (የኤሌክትሮኒክ ግብይትን) በማስቻል ለዲያስፖራ ማህበረሰቡ ትልቅ ሚናን ይጫወታል” ብለዋል።

የሞኔታ ቴክኖሎጂስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የምሩ ጫንያለው  “ከፍለተርዌቭ ጋር በመስራት ቴክኖሎጂዎቻችንን ተጠቅመን ለዲያስፖራ ማህበረሰቡ፣ ለደንበኞቻችን እንዲሁም ለነጋዴዎች ድንበር ተሻጋሪ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎትና ንግድን እውን ለማድረግ በጣም ጓግተናል። እንከን የለሽና ተጓዳኝ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎትን ለመፍጠር ያደረግነው ጥረታችን በኢትዮጵያ በተለያየ የኢኮኖሚ ደረጃ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ይጨምራል” ሲሉ ተናግረዋል።

አዲሱን አገልግሎት በመጠቀም ክፍያ ለመፈፀም ከኢትዮጵያ ውጪ ያለው ላኪ የተቀባዩን መረጃ፣ የክፍያውን መዳረሻ (አሞሌ ዲጂታል ዋሌት፣ የባንክ ሂሳብ ወይንም የገንዘብ ማውጫ ቦታዎች) እንዲሁም መዳረሻው ፈቃድ ያለው የአሞሌ ወኪል ከሆነ ተቀባዩ ገንዘቡን ለመውሰድ የሚያስችሉትን የደህንነት ጥያቄ እና መልስ ማስገባት ይጠበቅበታል።

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram