Select Page

የኢትዮጵያ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ ባለሙያዎች ማህበር 4ተኛ ዓመታዊ ጉባኤውን በዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት አካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ ባለሙያዎች ማህበር 4ተኛ ዓመታዊ ጉባኤውን በዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት አካሂዷል፡፡
ዳሸን ባንክ ስፓንሰር ያደረገው ጉባኤው የማህበሩ ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም እና ቀጣይ እቅዶቹ ላይ ተወያይቷል።

የማህበሩን አመታዊ የስራ አፈጻጸም ሪፓርት ያቀረቡት የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ አንዋር አብደላ በበጀት ዓመቱ ከወለድ ነጻ የፍይናንስ አገልግሎት ዘርፍ ለመደገፍ በርካታ ስራዎች እንደተከናወኑ አብራርተዋል። ከባንኮች ኢንሹራንስ ኩባንያዎች እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር የተከናወኑ ሰፊ ስራዎችን የገለጹት አቶ አንዋር ለዘርፉ ባለሙያዎች የተለያዩ ስልጠናዎች መስጠት እንደተቻለም ተናግረዋል ።

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ለተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት አስተዋፅዖ ላበረከቱ የማህበሩ አባላትና ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የማህበሩ ፕሬዝደንት አቶ ኢብራሂም ዳውድ በበኩላቸው ማህበሩ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ አገልግሎትን በኢትዩጵያ በተሻለ የማስተዋወቅ ግብ ይዞ እየሰራ መሆኑን የገለጹ ሲሆን የዘርፉ ማደግ በሐገር ኢኮኖሚያዊ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።

ዳሸን ባንክ ጉባኤውን ስፓንሰር በማድረግና ለዘርፉ እድገት እያበረከተ ላለው አስተዋጽኦ ምስጋና የሚቸረው እንደሆነም በጉባኤው ላይ ተመልክቷል ።

ዳሸን ባንክ የወለድ ነፃ የፍይናንስ ዘርፍ እንዲያድግ የበኩሉን አስተዋፅዖ እያደረገ ይገኛል። ባንኩ የማህበሩ (EIFFPA) ተቋማዊ አባል ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃም The Accounting and Auditing Organization for Islamic Financial Institutions (AAOIFI) ቋሚ አባል ነው

 

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram