ምርጥ አስሮችን ለመምረጥ የሚካሄደው ውድድር ዛሬ ነሐሴ 23 2014 ዓም በዳሸን ባንክ ዋናው መ/ቤት ተጀምሯል።
ከተለያዩ ከተሞች ከተውጣጡ ሰላሳ አምስት ተወዳዳሪዎች ውስጥ ምርጥ አስሮችን ለመምረጥ የሚካሄደው ውድድር ዛሬ ነሐሴ 23 2014 ዓም በዳሸን ባንክ ዋናው መ/ቤት ተጀምሯል።
ከሀዋሳ፣ ከድሬደዋ፣ ከአዳማ፣ ከደሴ እና ከባህርዳር የስልጠናና የውድድር ማዕከላት የተውጣጡ የስራ ፈጠራ ተወዳዳሪዎች ወደ ምርጥ አስር ለመግባት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።
በዚህ ውድድር ለሀገር እና ለወገን ጠቃሚ እንዲሁም ችግር ፈቺ የሆኑ የስራ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ተለይተው ወደ ምርጥ አስር ያልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።