Press Releases

የዳሸን ባንክ ባለአክሲዮኖች አመታዊ ጉባኤ ስኬታማ በሆነ መልኩ ተካሄደ
ባንኩ በዚህ ጉባኤ ጊዜያቸዉን ባጠናቀቁ የቦርድ አባላትን በአዳዲስ አባላት እንዲተኩ አድርጓል፡፡ በጉባኤዉ የባንኩ የካፒታል መጠን ከ3.5 ቢሊየን ወደ 5.5 ቢሊየን እንዲያድግ መደረጉም ተመልክቷል፡፡

ዳሸን ባንክ ለገበታ ለሃገር ፕሮጅክቶች ማስፈጸሚያ የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
ዳሸን ባንክ ገበታ ለሀገር በሚል ስያሜ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲተገበሩ በመንግስት ለታቀዱ ግዙፍ የልማት ፕሮጅክቶች ማስፈጸሚያ ይሆን ዘንድ የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
በያዝነው ዓመት “ገበታ ለሃገር’’ በሚል ጎርጎራ፣ወንጪና ኮይሻን የማስዋብ ፕሮጀክቶች እንደተጀመሩ ይታወቃል።

ዳሸን ባንክ ለተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር 3 ሚሊየን ብር አበረከተ
ባንኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “አዲሱን አመት በአዲስ ተስፋ ብርሃን” በሚል መሪ ቃል ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ በከተማው የሚገኙ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን ለማገዝ ድጋፉን አበርክቷል፡፡
ዳሸን ባንክ ባለፈው አመት ለዚሁ መርሃ ግብር 1 ሚሊዮን አንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር ማበርከቱ ይታወሳል፡፡

ዳሸን ባንክ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎችን በአዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች ከፈተ
ዳሸን ባንክ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎችን በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ከፍቷል። ባንኩ በቤተል አካባቢ ተቅዋ በሚል ስያሜ ካስመረቀው ቅርንጫፍ በተጨማሪ በአዲስ አበባ መርካቶ ጣና ገበያ ውስጥ አንዋር፣ በሀረር ከተማ አንሷር፣ በጅግጅጋ ጋራድ ዊልዋል፣ በጦራ ከተማ ጦራ የተሠኙ ተጨማሪ አዳዲስ ቅርንጫፎችን ለአግልግሎት ክፍት አድርጓል።

ዳሸን ባንክ በላልይበላ ከተማ ላይ በተቋቋመው በዕፅዋት ዓለም የዕፅዋት ማደጎ መርሃ ግብር ላይ ከግል ተቋማት ብቸኛ የፕላቲኒየም ስፖንሰር በመኾኑ ፤ በፕሮጀክቱ ሥም ከክብርት ዶክተር ሂሩት ካሳው እጅ የእውቅና ሰርቲፊኬት ተበርክቶለታል ።
ዳሸን ባንክ በላልይበላ ከተማ ላይ በተቋቋመው በዕፅዋት ዓለም የዕፅዋት ማደጎ መርሃ ግብር ላይ ከግል ተቋማት ብቸኛ የፕላቲኒየም ስፖንሰር በመኾኑ ፤ በፕሮጀክቱ ሥም ከክብርት ዶክተር ሂሩት ካሳው እጅ የእውቅና ሰርቲፊኬት ተበርክቶለታል ።

የዳሸን ባንክ ከፍተኛ አመራር አባላት እንጦጦ በሚገኘው የባንኩ የተፈጥሮ ፓርክ አገር በቀል ችግኞችን ተክለዋል
የዳሸን ባንክ ከፍተኛ አመራር አባላት እንጦጦ በሚገኘው የባንኩ የተፈጥሮ ፓርክ አገር በቀል ችግኞችን ተክለዋል፡፡ ዳሸን ባንክ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኀበር የአልማዝ አባል ሲሆን ከማህበሩም ጋር በመተባበር የአካባቢ እንክብካቤ ተግባራት እየሠራ ይገኛል፡፡

ዳሸን ባንክ የአብሮነት እና የምስጋና ቀንን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ከሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ጋር እንዲሁም በሚሊኒየም አዳራሽ ከሚገኙ የኮቪድ 19 ህሙማን ጋር የአዲስ ዓመት ዋዜማን አከበረ።
ዳሸን ባንክ የአብሮነት እና የምስጋና ቀንን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ከሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ጋር እንዲሁም በሚሊኒየም አዳራሽ ከሚገኙ የኮቪድ 19 ህሙማን ጋር የአዲስ ዓመት ዋዜማን አከበረ።

ዳሸን ባንክ በህንፃዎች ላይ ተከራይተው ለሚገኙ ተከራዮቹ የ 50% ቅናሽ አደረገ
ዳሸን ባንክ አ.ማ. በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ አርባ ምንጭ፣ ሐዋሳ፣ ባህርዳር፣ ደብረብርሃን፣ ደሴ፣ ዲላ፣ ድሬዳዋ፣ ጎንደር፣ ኮምቦልቻ፣ ወልዲያ፣ ወላይታ፣ ቦንጋ እና ጅማ ከተሞች ላይ በሚገኙ 19 ህንጻዎች ላይ ተከራይተው ለሚገኙ ተከራዮቹ የ50% ቅናሽ አደረገ፡፡

ዳሽን ባንክ የ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ መከላከያ ዝግጅት አበረከተ
ዳሽን ባንክ ለኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ መከላከል ዝግጅት የሚውል ገንዘብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን ለማሰባሰብ የቀረበውን አገራዊ ጥሪ ተከትሎ ፤ በመንግሥት ለተቋቋመዉ ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ የብር 10,000,000.00 (አስር ሚሊዮን ብር) ድጋፍ ለገሰ ።