Select Page

በተመረጡ ቅርንጫፎች ለሙከራ ጊዜ የተመጀረዉ የተጨማሪ ሰዓት አገልግሎት ወደቋሚነት ተሸጋገረ

ዳሸን ባንክ በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ የተወሰኑ ቅርጫፎች ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ እስከ ምሽቱ አንድ ስዓት በ110 ቅርንጫፎች እንዲሁም ከእሁድ እስከ እሁድ በ22 ቅርንጫፎች የሙከራ አገልግሎት ሲሰጥ  የቆየ ሲሆን ይህንንም  ወደቋሚነት አሸጋግሯል፡፡

የባንኩ ችፍ ሪቴልና ብራንች ባንኪንግ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ይህንዓለም አቅናዉ ይህን አስመልክተዉ ባስተላለፉት መልዕክት  ባንኩ በሙከራ ጊዜው ባደረገው ግምገማ ከሰራተኞች እና ከደንበኞች አበረታች ምላሾች ያገኘ በመሆኑ የሙከራ ጊዜውን ቀደም ብለው በተመረጡ እና በሙከራ ፕሮግራሙ በተሳተፉ ቅርንጫፎች ወደ ቋሚ የአገልግሎት ፕሮግራም ያሸጋገረ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

አቶ ይህንዓለም በሙከራ ጊዜዉ በራሳቸዉ ተነሳሽነት ለመርሃግብሩ ስኬት ከፍተኛ ያበረከቱ ሰራተኞችንና የስራ መሪዎች አመስግነዋል፡፡

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram