Select Page

የስብሰባ ጥሪ

ለዳሸን ባንክ አ.ማ. ባለአክስዮኖች በሙሉ

የዳሽን ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች ሃያ ስምንተኛ መደበኛ እና ሃያ አምስተኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ሕዳር 9 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ሳርቤት በሚገኘው መቻሬ ሜዳ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በስብሰባው ላይ እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፡ –

  1. ድምÒ ቆጣሪዎችን መሰየምና ማÒደቅ
  2. ምዕላተ ጉባዔውን ማረጋገጥ
  3. የስብሰባ አጀንዳውን ማÒደቅ
  4. አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና ነባር አክሲዮኖችን ግዥና ዝውውሮችን ማፅደቅ
  5. የዳይሬክተሮች ቦርድ አመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ
  6. የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥ እና ማፅደቅ
  7. የውጭ ኦዲተሮች መcምና ክፍያቸውን መወሰን
  8. በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተወያይቶ መወሰን
  9. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ክፍያና አበል መወሠን፤
  10. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማÎደቅ

አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1. ድምÒ ቆጣሪዎችን መሰየምና ማÒደቅ
  2. ምዕላተ ጉባዔውን ማረጋገጥ
  3. የስብሰባ አጀንዳውን ማÒደቅ
  4. የዳሸን ባንክ አ.ማ. የመመስረቻ ፅሁፍን ስለማሻሻል
  5. የባንኩን ካፒታል ስለማሳደግ በቀረበው የውሳኔ ኃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሠን
  6. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማÒደቅ

ማሳሰቢያ

  • በጉባኤው ላይ በግንባር መገኘት የማይችሉ ከሆነ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፊት ለፊት በሚገኘው የዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ የቦርድ Ò/ቤት በመቅረብ የውክልና ቅÒ በመሙላት ከስብሰባው ከሶስት ቀን በፊት ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
  • በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡም ሆነ በጉባኤው በአካል የምትገኙ ባለአክስዮኖች ማንነታችሁን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውን እና ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እንዲሁም በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ህጋዊ ውክልና ይዛችሁ ለምትቀርቡ ተወካዮች የወካያችሁን ማንነት የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
  • በውል አዋዋይ የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ ዋና ማስረጃውን እና ኮፒውን ይዞ በመቅረብ በስብሰባው ላይ መሳተፍ ይችላል፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ

ዳሸን ባንክ አ.ማ.

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram