Select Page

የዳሸን ባንክ ሁለተኛው ዙር የስራ ፈጠራ ስልጠናና ውድድር መርሃግብር አካል የሆነ የአቅም ግንባታ ስልጠና በድሬዳዋ ከተማ ተደረገ።

ለአምስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ስልጠና ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ሰልጣኞች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሰልጣኞቹ በስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች ባህሪያት፣ በንግድ ስራ ዕቅድ አዘገጃጀት፣ በጊዜ አጠቃቀም፣ አነስተኛ ድርጅቶችን በማስተዳደር ክህሎት፣ በግለሰብ ገንዘብ አስተዳደር፣ በድርጅት ገንዘብ አስተዳደርና በባንክ አገልግሎት ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና ወስደዋል፡፡

ዳሸን ባንክ በድሬዳዋ ከተማ ለሥራ ፈጣሪዎች ሲሰጥ የቆየውን ሥልጠና ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የባንኩ ቺፍ ፋይናንስ ኦፊሰር አቶ አለምነህ አበበ ተገኝተው ለሰልጣኞችና ለመርሃ ግብሩ አስተባባሪዎች የዕውቅና ሰርተፊኬት ሰጥተዋል። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይና የአስተዳደሩ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ለሰልጣኞች መልዕክት አስተላልፈዋል። የተመረጡ የዳሸን ባንክ ደንበኞች ባንኩ ስላደረገላቸው ድገፍ ምስክርነታቸውን ለታዳሚው አጋረተዋል። በስልጠናው ለተካፈሉ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች የዳሸን ባን ድሬዳዋ ቀጠና ጽ/ቤት ስጦታ አበርክቷል። መሰል የስልጠናና ውድድር መርሃ ግብሮች በሌሎች ከተሞችም ይከናወናሉ።

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram