የዳሸን ባንክ ባለአክሲዮኖች አመታዊ ጉባኤ ስኬታማ በሆነ መልኩ ተካሄደ
የዳሸን ባንክ ባለአክሲዮኖች 27ኛ መደበኛና 24ኛ ድንገተኛ አመታዊ አመታዊ ጉባኤ የኮሮና ቫይረስን ስርጭት መከላከል በሚያስችልና ስኬታማ በሆነ መልኩ በተንጣለለዉ መቻሬ ሜዳ ተካሄደ፡፡
ባንኩ በዚህ ጉባኤ ጊዜያቸዉን ባጠናቀቁ የቦርድ አባላትን በአዳዲስ አባላት እንዲተኩ አድርጓል፡፡ በጉባኤዉ የባንኩ የካፒታል መጠን ከ3.5 ቢሊየን ወደ 5.5 ቢሊየን እንዲያድግ መደረጉም ተመልክቷል፡፡ ባንኩ ባለፈዉ አመት ከግብር በፊት 1.8 ቢሊየን ብር ማትረፉንም አስታዉቋል፡፡ ዳሸን ባንክ ባለፈዉ በጀት አመት ብቻ የተለያዩ ማህበራዊ ሃላፊነቶቹን ለመወጣት ከ92.4 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ አድርጓል፡፡
በባንኩ ባለፈዉ አመት ብቻ ከ148 ሺ በላይ አዳዲስ ከወለድ ነፃ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሂሳብ የከፈቱ ሲሆን ይህም ባንኩን ከ2.4 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ እንዲያገኝ አስችሎታል፡፡ ባለፈዉ በጀት አመት ከ46 ቢሊየን ብር በላይ ብድር የተለያዩ ደንበኞች እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ በበጀት አመቱ ከ1.1 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ አዳዲስ ደንበኞችም የዳሸን ባንክ ኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን አካዉንት ከፍተዋል፡፡ የባንኩ የካርድ ተጠቃሚዎች ቁጥርም ከ1.1 ሚሊየን በላይ የደረሰ ሲሆን ይህም ካለፈዉ አመት ጋር ሲነፃፀር የ25.5 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ የሃብት መጠን 68.3 ቢሊየን ብር የደረሰ ሲሆን ይህም ካለፈዉ አመት ጋር ሲነፃፀር ከ21 በመቶ በላይ ዕድገት አሳይቷል፡፡
ዳሸን ባንክ ባለፈዉ አመት በመላ አገሪቱ ያሉትን የቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 423 አሳድጓል፡፡