የዳሸን ባንክ ከፍተኛ አመራር አባላት እንጦጦ በሚገኘው የባንኩ የተፈጥሮ ፓርክ አገር በቀል ችግኞችን ተክለዋል
የዳሸን ባንክ ከፍተኛ አመራር አባላት እንጦጦ በሚገኘው የባንኩ የተፈጥሮ ፓርክ አገር በቀል ችግኞችን ተክለዋል፡፡ ዳሸን ባንክ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኀበር የአልማዝ አባል ሲሆን ከማህበሩም ጋር በመተባበር የአካባቢ እንክብካቤ ተግባራት እየሠራ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ባለፉት በርካታ አመታት ለባንኩ በተከለለው የእንጦጦ ፓርክ ሠራተኞቹን በማስተባበር አገር በቀል ችግኞችን ሲያለማ እንደነበርም ይታወቃል