ዳሸን ባንክ ለተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር 3 ሚሊየን ብር አበረከተ
ባንኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “አዲሱን አመት በአዲስ ተስፋ ብርሃን” በሚል መሪ ቃል ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ በከተማው የሚገኙ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን ለማገዝ ድጋፉን አበርክቷል፡፡
ዳሸን ባንክ ባለፈው አመት ለዚሁ መርሃ ግብር 1 ሚሊዮን አንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር ማበርከቱ ይታወሳል፡፡ ባንኩ ባለፈው በጀት አመት በአጠቃላይ 170 ሚሊየን ብር ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች አውሏል ፡፡