Select Page

ዳሸን ባንክ ለገበታ ለሃገር ፕሮጅክቶች ማስፈጸሚያ የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ዳሸን ባንክ ገበታ ለሀገር በሚል ስያሜ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲተገበሩ በመንግስት ለታቀዱ ግዙፍ የልማት ፕሮጅክቶች ማስፈጸሚያ ይሆን ዘንድ የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
በያዝነው ዓመት “ገበታ ለሃገር’’ በሚል ጎርጎራ፣ወንጪና ኮይሻን የማስዋብ ፕሮጀክቶች እንደተጀመሩ ይታወቃል። ለሦስቱ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ቢያንስ ስድስት ቢሊዮን ብር ያህል እንደሚያሰፈልግም በመንግሥት ተነግሯል፡፡ ዳሸን ባንክም ለነዚህ ለሶስቱ ፕሮክቶች ለእያንዳንዳቸዉ 10 ሚሊየን ብር በአጠቃላይ 30 ሚሊየን ብር እንደሚለግስ ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ተናግረዋል፡፡

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram