ዳሸን ባንክ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎችን በአዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች ከፈተ
ዳሸን ባንክ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎችን በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ከፍቷል። ባንኩ በቤተል አካባቢ ተቅዋ በሚል ስያሜ ካስመረቀው ቅርንጫፍ በተጨማሪ በአዲስ አበባ መርካቶ ጣና ገበያ ውስጥ አንዋር፣ በሀረር ከተማ አንሷር፣ በጅግጅጋ ጋራድ ዊልዋል፣ በጦራ ከተማ ጦራ የተሠኙ ተጨማሪ አዳዲስ ቅርንጫፎችን ለአግልግሎት ክፍት አድርጓል።
ባንኩ ከዚህ ቀደም ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ በአዳማ ከተማ በረካ ፣ በድሬዳዋ ቡኻሪ ፣ በደሴ መሐመድ አል-አሙዲ የተሰኙ ቅርንጫፎችን ከፍቶ ለደንበኞቹ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት በባንኩ ውስ|ጥ ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት ብቻ የሚሰጡ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 8 (ስምንት) አድርሷል፡፡ በነዚህ ቅርንጫፎቹ ባንኩ ደንበኛውን ማዕከል ያደረገ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርገው የተደራጁ ናቸው፡፡ ዳሸን ባንክ በዚህ የበጀት ዓመት ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 12 ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል፡፡