Select Page

ዳሸን ባንክ ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

ዳሸን ባንክ ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

ዳሸን ባንክ ከፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር በሰነድ ማረጋገጥና ምዝገባ  እንዲሁም  ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ባንኩን በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት የዳሸን ባንክ ቺፍ ሪቴይልና ኤም ኤስ ኤም ኢ ኦፊሰር አቶ ጥበቡ ሰለሞን እንዳሉት ፤ የባንክ ትልቁ ተግባር ከሰነድ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ዳሸን ባንክ ኤጀንሲዉን ስትራቴጂክ አጋር አድርጎ ለመሥራት ይፈልጋል ፡፡ ባንኩ ከኤጀንሲዉ ጋር በጋራ የሚሠራቸዉን ሥራዎች ለወደፊት በመነጋገር ይበልጥ ያሰፋል ፤ ብለዋል ፡፡

የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ በበኩላቸዉ፤  ዳሸን ባንክ ኤጀንሲዉ በጋራ ለመሥራት ላቀረበዉ ጥያቄ ከሁሉም ቀድሞ ምላሽ በመስጠቱ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ከዳሸን ባንክ ጋር በትብብር ለመሥራት የተደረሰዉ ስምምነት በዘርፉ የሚስተዋለዉን የሰነድ ማጭበርበር ተግባር ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋልም ብለዋል፡፡ ስምምነቱ ደንበኞች የሰነድ ማረጋገጫና ምዝገባ ክፍያዎችን በዳሸን ባንክ በኩል በመክፈል በቀላሉ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነዉ፡፡

የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በአዲስ አበባ 14 ቅርንጫፎች እንዲሁም በድሬዳዋ 1 ቅርንጫፍ ከፍቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ፡፡

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram