Select Page

ዳሸን ባንክ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ከወለድ ነፃ ፋይናንስ አቀረበ

ዳሸን ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ሸሪክ የተሰኘ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በማስተዋወቅ አገልግሎት የጀመረው ከ5 ዓመት በፊት ነበር፡፡ ይህም ባንኩ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች አካታች መሆኑን ያሳየበት ሆኗል፡፡

ይህ የባንክ አገልግሎት የዛሬ አምስት ዓመት ሲጀመር በዘርፉ በቂ ልምድና ክህሎት የሌለ በመሆኑ ከፍተኛ ዝግጅት የጠየቀ ነበር፡፡ የራሱ የሆኑ የፖሊሲና አሰራር ማዕቀፎችና ማዘጋጀትና መዘርጋት፣ በዘርፉ የሚሰማራውን የሰው ሃይል ማብቃት የአገልግሎቱን ልዩ ምልክት ማዘጋጀትና ሌሎችም የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን  ባንኩ ሰፊ ጊዜ ወስዶ አከናውኗቸዋል፡፡

ይህም ምንም እንኳን በዘርፉ የሚሰጠው አገልግሎት አዲስና አጭር ዕድሜ ያለው ቢሆንም ዳሸን ባንክ በአጭር ጊዜ ተቀባይነቱን በማስፋት በርካታ ስኬቶችን እንዲያስመዘግብ አስችሎታል፡፡ ዳሸን ባንክ አገልግሎቱን የጀመረው ራሱን የቻለ የሸሪዓ አማካሪ ምክር ቤት በማቋቋም ነበር፡፡

ከአምስት ዓመታት በፊት በአንድ መስኮት መሰጠት የተጀመረው ይህ አገልግሎት ዛሬ ላይ ከፍተኛ ዕድገት በማሳየት በ62 ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አግልግሎት በሚሰጡ ቅርንጫፎች አገልግሎት በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ 700 በሚሆኑ ቅርንጫፎች በአንድ መስኮት አገልግሎቱ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ ዛሬ ላይ የዳሸን ሸሪክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከ600 ሺ በላይ የሆኑ ሲሆን ባንኩ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ችሏል፡፡

ዳሸን ባለፉት 5 ዓመታት በዚህ ዘርፍ ብቻ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ለተሰማሩ ደንበኞቹ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ማበደር ችሏል፡፡ ባለፈው ዓመት ብቻ ባንኩ በዚህ ዘርፍ የሰጠው የብድር መጠን ከ4.3 ቢሊየን ብር በላይ የነበር ሲሆን ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ92.3 በመቶ ዕድገት ያሳየ ነበር፡፡

ባንኩ በዘርፉ ተደራሽነቱንና አካታች አገልግሎቶችን ከመስጠት አልፎ ዘርፉ የሚጠይቀውን ስነ-ምግባር ተግባራዊ በማድረግ ተጠቃሽ ሚና ተጫውቷል፡፡  ወደፊትም ባንኩ ማህበረሰባችንን ከአገልግሎቱ ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያደገውን ርብርብ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram