Select Page

ዳሽን ባንክና ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ያስገነቡት የምገባ ማዕከል  ተመረቆ ሥራ ጀመረ

ዳሽን ባንክና ሜድሮክ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋራ በመተባበር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም አካባቢ  በ25 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነቡት ተስፋ ብርሃን አሙዲ  3ኛ ቅርንጫፍ የምገባ ማዕከል የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋ ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡

በምርቃው ሥነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አባቤ እንደገለጹት የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራቸው  ሰው ተኮር  የልማት ሥራዎቸ  መካከል በከተማዋ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች   ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በተመረጡ የከተማዋ ቦታዎች ምገባ ማዕከላት ማቋቋም ነው፡፡ በዚሁ መሰረት  ዳሽን ባንክና ሜድሮክ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋራ በመተባበር ተስፋ ብርሃን አሙዲ ቅርንጫፍ የተሰኘ የምገባ ማዕከልን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ  ግንብቶ ለፍሬ በማብቃት  በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉና በአሁኑ ጊዜ ለከፋ ችግር የተጋለጡ  የአካባቢው ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

 ማዕከሉ በአካባቢው ለሚኖሩ 30 ሴቶች ቋሚ የሥራ እድል እንደሚፈጥም  ከንቲባዋ ጠቁመዋል፡፡

የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል  መሀመድ በበኩላቸው ድርጅታቸው ከዳሻን ባንክ ጋራ በመተባበር ቀደም ብሎ ሁለት የምገባ ማእከላትን በአዲስ ከተማና በልደታ ክፍለ ከተማ በመገንባት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውሰው አሁን በለሚ ኩራ የተገነባውን ተሰፋ ብርሃን  አሙዲ ቅርንጫፍ የምገባ ማዕከል ግንብቶ ከማጠናቀቅ በተጨማሪም በየአመቱ ለምገባ የሚወጣውን 25 ሚሊዮን ብር የሚሆን  ወጪ  ድርጅታቸው ከዳሽን ባንክ ጋር በመሆን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ በዕለቱ ዳሽን ባንክ ለምገባ ማዕከሉ ግንባታ ለአበረከተው አስተዋጽኦ የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram