Select Page

ዳሸን ባንክ የ6ኛውን የታማኝ የግብር ከፋዮች ሽልማት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ

ዳሸን ባንክ በሐገር አቀፍ ደረጃ ለ6ተኛ ጊዜ በተዘጋጀው የታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር ላይ የፕላቲኒየም ደረጃ ሽልማትን ተቀብሏል፡፡

የ6ኛው ዙር የታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ሥነ-ስርዓት በትላንትናው እለት በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ተካሒዷል፡፡

በዚሁ ፕሮግራም ላይ 550 ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ያገኙ ሲሆን ግብር ከፋዮች በሀገር ውስጥ ገቢ በ12 እና በጉምሩክ በ7 የመምረጫ መስፈርቶች መሰረት ተመዝነው እውቅናው ተሰጥቷቸዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ የባንኩን የፕላቲኒየም ደረጃ እውቅናና ሽልማቱን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተቀብለዋል ፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል ።

 

 

 

 

 

 

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram