Select Page
ዳሽን ባንክ የ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ መከላከያ ዝግጅት አበረከተ

ዳሽን ባንክ የ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ መከላከያ ዝግጅት አበረከተ

ዳሽን ባንክ የ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ መከላከያ ዝግጅት አበረከተ

(አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22 ቀን 2012 ዓ.ም) ዳሽን ባንክ ለኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ መከላከል ዝግጅት የሚውል ገንዘብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን ለማሰባሰብ የቀረበውን አገራዊ ጥሪ ተከትሎ ፤ በመንግሥት ለተቋቋመዉ ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ የብር 10,000,000.00 (አስር ሚሊዮን ብር) ድጋፍ ለገሰ ።

በቅርቡ “ የኅብረተሰብ ጤና የአገር ደኅንነትና ዕድገት መሠረት ነው ” በሚል መሪ ቃል ባንኩ የወስዳቸውን የማኅበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ግዴታዎች ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው ፡፡ ይህም  ደንበኞችን ከአካላዊ ንክኪ ርቀዉ የባንክ አገልግሎት እንዲያገኙ ከሚያስችሉ ዕርምጃዎች መካከል ኤ.ቲ.ኤም. ማሽኖችን ተጠቅመው ክፍያ በሚፈጽሙ ደንበኞች ላይ ይተገበር የነበረውን የኮሚሽን ክፍያ ሙሉ በሙሉ በማንሳት በነፃ ክፍያ እንዲያከናወኑ ፣ ምርቶችን ከውጭ የሚያስገቡ ደንበኞች የሚያጋጥማቸውን የንግድ እንቅስቃሴ መስተጓጎል ከግምት ውስጥ በማስገባት ፤ ከዚህ በፊት ለባንክ መተማመኛ ሰነድ ብድር ወይም ለኤል.ሲ. ማራዘሚያ ይከፍሉ የነበረው ኮሚሽን ተነስቶ ነፃ እንዲሆን ፣  በቀጥታ የግዢ ትዕዛዝ ሰነድ ከውጭ ምርት ለሚያስገቡ ደንበኞች ለጊዜ ማራዘሚያ ይከፈሉ የነበረው ኮሚሽን በ 50 በመቶ እንዲቀንስ  ፣ የተበዳሪ ደንበኞች የንግድ እንቅስቃሴ ወረርሽኙ በሚፈጥረው ተፅዕኖ ምክንያት እንደሚቀዛቀዝ በመገመት ፤ የተመላሽ ብድሮች የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው ደንበኞች ጥያቄ በሚያቀርቡበት ወቅት ይከፍሉ የነበረው ኮሚሽን ተነስቶ በነፃ እንዲስተናገዱ ፣ ደንበኞች ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ ሳይሔዱ የቪዛና የወለድ አልባ አገልግሎት የክፍያ ካርዶቻቸዉን በኤ.ቲ.ኤም. ማሽኖች ሲጠቀሙ  በየቀኑ የሚያወጡት ገንዘብ ላይ እጥረት እንዳያጋጥማቸዉ የዕለት ብር ወጪ መጠን ገደቡ ላይ ማሻሻያ በማድረግ ወደ አሥር ሺሕ ብር ከፍ እንዲል ሲያደርግ ፤ ባንኩ ወደ ፊትም  የወቅቱን ሁኔታ እያገናዘበ ተመሳሳይ እርምጃወችን እንደሚወስድ ማስታወቁ የሚታወስ ነው ፡፡

በዚሁም መሠረት ከላይ ከተጠቀሱት ከፍተኛ ዉሳኔዎች በተጨማሪ ዳሸን ባንክ ወረርሽኙ በህዝባችን ላይ የሚያሳድረውን የጤናና የኢኮኖሚ ተጽዕኖዎች በመገምግም ፤ ደንበኞቹንና ዜጎቻችንን የሚደግፍ ተመሳሳይ እርምጃዎችን እንደሚውስድ የገባውን ቃል በመጠበቅ ፤ የዳሽን ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የወሰነዉን የአሥር ሚሊዮን ብር ድጋፍ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ለብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው የኃብት ማሰባሰብ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ አስረክበዋል ።

ዳሸን ባንክ ሁልጊዜም አንድ እርምጃ ቀዳሚ!

Dashen Bank contributes 100,000 exercise books for Addis Ababa City Administration

Dashen Bank contributes 100,000 exercise books for Addis Ababa City Administration

Dashen Bank contributes 100,000 exercise books for Addis Ababa City Administration

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram