
ዳሸን ባንክ የተሳተፈበት ግራንድ ኢትዮ ኢድ ኤክስፖ ተከፈተ
ዳሸን ባንክ የተሳተፈበት ግራንድ ኢትዮ ኢድ ኤክስፖ ተከፈተ
Dashen Bank Hosts Grand Iftar to Celebrate Ramadan
– Launches “Be Sharik for a Social Cause” Initiative
Addis Ababa, March 11, 2025 –
Dashen Bank hosted a special Iftar program today at the Sheraton Addis Hotel, bringing together esteemed customers, partners, and stakeholders in celebration of the holy month of Ramadan. This event reflects the Bank’s deep commitment to fostering community engagement and strengthening relationships with its valued customers.
The event was graced by remarks from Dashen Bank’s CEO, Ato Asfaw Alemu, who extended heartfelt Ramadan greetings to the Bank’s customers and the broader Islamic community. He emphasized Dashen Bank’s dedication to providing Shari’ah-compliant banking solutions that align with customers’ values and financial needs.
Another key highlight of the evening was the launch of the “Be Sharik for a Social Cause” initiative, announced by the Chief Interest-Free Banking Officer. This impactful program aims to support charitable organizations and social causes by linking Dashen Bank customers’ interactions—such as account openings, deposit volumes, and POS transactions—to a structured contribution model. The initiative will run from February 2025 to June 2025, reinforcing the Bank’s commitment to financial inclusion and social responsibility.
As one of the leading interest-free banking service provider in Ethiopia, Dashen Bank recently celebrated the 7th anniversary of its Sharik Interest-Free Banking service. In line with its commitment to corporate social responsibility, the Bank allocated over 22 million birr from customer trust contributions to 31 charitable organizations across Ethiopia, demonstrating the transformative power of ethical banking.
With over 1.3 million customers benefitting from its interest-free banking services, Dashen Bank continues to uphold the values of unity, generosity, and inclusivity. The Bank remains steadfast in its mission to provide Shari’ah-compliant, customer-centric financial solutions while making a meaningful impact on communities nationwide.
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች-8) በሴቶች ብቻ አገልግሎት በሚሰጠው ዳሸን ኖክ ቅርንጫፍ በድምቀት ተከበረ
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች-8) በእንስቶች ብቻ አገልግሎት በሚሰጠው ዳሸን ባንክ ኖክ ቅርንጫፍ በድምቀት ተከበረ።
በመርሃግብሩ ላይ የዳሸን ባንክ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የባንኩ ደንበኞችና ሌሎች እንግዶች ታድመዋል።
የዳሸን ባንክ የደንበኞች አገልግሎት ዋና መኮንን (Chief Customer Experience Officer) እየሩሳሌም ዋጋው ባደረጉት ንግግር፣ ሴቶች በአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ሚና ቁልፍና ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
ይህንን የሴቶች ወሳኝነት የተረዳው ዳሸን ባንክ ለሴቶች ብቻ የተለየ አገልግሎት ከልዩ የወለድ ጥቅም ጋር አቅርቦ ሴት ደንበኞች እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ አስታውሰው፣ በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትም እንዲሁ ሴቶችን ተጠቃሚ ያደረገ አገልግሎት ማስተዋወቁን ተናግረዋል።
የዳሸን ባንክ ቺፍ ፒፕል ኦፊሰር ህይወቴ ከፈለኝ በበኩላቸው ዳሸን ባንክ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግና ሴቶች በሀገራቸው፣ በድርጅታቸው እንዲሁም በቤተሰባቸው የሚያበረክቱትን ጉልህ አስተዋፅኦ ለማሳደግ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ የሴቶችን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ ማዕቀፎችን በማካተት በባንኩ የሰው ኃይል ፖሊሲ ሴት ሰራተኞችን ማዕከል ያደረጉ እንዲሆኑ ፕሮግራም ቀርፆ ወደ ስራ ከገባ መቆየቱን አስታውቀዋል።
የተቀናጀ ሴቶችን የማብቃት ፕሮግራም “Comprehensive Women Empowerment Program” ቀርፆ ወደ ስራ ያስገባው ዳሸን ባንክ፣ በዚህም ሴቶችን ለስራ የማብቃት፣ የሴቶች ትስስር መፍጠር፣ እንዲሁም የሴቶች የምክክር ፕሮግራሞችን ቀርፆ ወደ ስራ በማስገባት በሁሉም መስክ የሴቶችን ተሳትፎ የማሳደግን እንቅስቃሴ በባንክ ደረጃ እያሳካ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ዳሸን ባንክ ከ22 ሚሊየን ብር በላይ ለግብረ-ሠናይ ድርጅቶች ለገሰ
°ከወለድ ነፃ አገልግሎት 7ኛ ዓመት ተከበረ
ዳሸን ባንክ ከደንበኞቹ በአደራ የሰበሰበውን ከ22 ሚሊየን ብር በላይ ለተለያዩ አገር-በቀል ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ለገሰ፡፡ ባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት (ሸሪክ) የጀመረበትን 7ተኛ ዓመት ዛሬ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች በዋናው መስሪያ ቤት አክብሯል፡፡
በዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ መስፍን በዙ ሸሪክ በሚል ስያሜ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የጀመረበትን 7ተኛ ዓመት ባከበረበት ዕለት ባደረጉት ንግግር አመኔታቸውን ለሠጡ ደንበኞች የላቅ ምስጋና እናቀርባለን ሲሉ ተናግረዋል።
ባንኩ በሚሰጠው ከወለድ ነፃ አገልግሎት ብቻ በአሁኑ ወቅት ከ1 ሚሊየን በላይ ደንበኞች ማፍራት ችሏል።
ዳሽን ባንክ የካቲት 26/2010 በአንድ መስኮት የጀመረው አገልግሎት አድጎ ከ80 በላይ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎችና ከ800 በላይ በሆኑ ቅርንጫፎች በመስኮት ለደንበኞቹ የተሟላ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት ለ 31 አገር-በቀል ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
ዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በሱማሌ ክልል ለሚገኙ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ከወለድ ነጻ በሆነ መንገድ 100 ሚሊየን ብር ተዘወዋዋሪ ብድር ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ በዛሬው ዕለትም ይህን ድጋፍ አስመልክቶ ዘጋቢ ፊልም ለዕይታ ቀርቧል፡፡
የባንኩ ከወለድ ነፃ አገልግሎት (ሸሪክ) እ.ኤ.አ ህዳር 28 ቀን 2023 በባህሬን ማናማ በተካሄደው 9ኛው የኢስላሚክ ሪቴል ባንክ ሽልማት ላይ ጠንካራ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኢትዮጵያ የሚሠጥ ባንክ (The Strongest Islamic Retail Banking Window in Ethiopia ) በሚል ዕውቅና አግኝቷል፡፡
ዕውቅናውን የሰጠው ለንደን በሚገኘውና በፋይናንስ ዘርፍ ጥናትና ምርምር የሚሰራው ኬምብሪጅ አይ ኤፍ ኤ(Cambridge IFA) የተሰኘ ተቋም ነው፡፡
ባንኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ የእስላማዊ ፋይናንስ ተቋማቶችን የሂሳብ፣ ኦዲት እና ሸሪዐህ መስፈርቶችን የሚያወጣው ተቋም (The Accounting and Auditing Organization For Islamic Financial Institutions) አባል የሆነ በኢትዮጵያ ብቸኛው የፋይናንስ ተቋም ነው።
በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የግል ባንክ የሆነው ዳሸን ባንክ ለትርፍ ካልተቋቋመው ዓለም አቀፍ ድርጅት አክሲዮን (Accion) እና ማስተርተካርድ ሴንተር ፎር ኢንክሉሲቭ ግሮውዝ ጋር በመተባበር የአነስተኛ ቢዝነሶችን የፋይናንስ ፍላጎት በዲጂታል አገልግሎት ለማሟላት የሚያሰችል አዲስ የኢኖቬሽን የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም ስምምነት አደረጉ፡፡
በዚህ ስምምነት መሰረት አክሲዮን ዳሸን ባንክ ለጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራዞች የዲጂታል ባንክ አገልግሎትና በተለይም በሴቶች ባለቤትነት የሚመሩ ቢዝነሶችን ለመደገፍ ለሚያቋቁመው የኢኖቬሽን ልህቀት ማዕከል ግንባታ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
በኢትዮጵያ ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚደርሱ የአነስተኛ፣ መካከለኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ኢኮኖሚውን በማንቀሳቀስ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ሲሆኑ ነገር ግን ከዚህ ውስጥ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑት 1.9 በመቶ አነስተኛ እና 6 በመቶ ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ብቻ ናቸው፡፡በአገሪቱ በጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራዞች ዘርፍ ያለው የፋይናንስ ክፍተት 4.2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን ይገመታል።ሥራ አጥነት፣ አነስተኛ ገቢ እና የፋይናንስ ግንዛቤ እጥረት ለመደበኛ የፋይናንስ አገልግሎት እጦት ቁልፍ ምክንያቶች ሆነው ቆይተዋል።ከዚህም በላይ 55 በመቶ ከሆነው የወንዶች ድርሻ ጋር ሲነፃፀር በመደበኛ የፋይናንስ ተቋም ውስጥ የባንክ ሂሳብ (አካውንት) ያላቸው ሴቶች 39 በመቶ ብቻ ሲሆኑ ይህም እያደገ በመጣው የዲጂታል ፋይናንስ ስነ-ምህዳር እንዳይጠቀሙ ከማድረጉም በላይ እና ለአገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ገድቦታል፡፡
ዳሸን ባንክ በኢትዮጵያ አዳዲስ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ ግንባር ቀደም ሆኖ ቆይቷል።በተለይም የአነስተኛ ቢዝነስ ባለቤቶች እንከን አልባ የገንዘብ ልውውጥ እንዲያደርጉ የሚያግዛቸውን የዲጂታል ዋሌት በቅድሚያ ካስተዋወቁ ባንኮች ዳሸን ቀዳሚው ነው፡፡አሁንም ከአክሲዮን ጋር በመሆን የሚገነባው የኢኖቬሽን ልህቀት ማዕከል በዋናነት ዓላማ ያደረገው በኢትዮጵያ በተለምዶ በጥሬ ገንዘብ ላይ ተንጠልጥለው አገልግሎታቸውን የሚያቀርቡትንና ጥቂት ንብረቶች ያላቸው በተለይም በትላልቅ ባንኮች ዕይታ ውስጥ ላልገቡ የአነስተኛ፣ መካከለኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች አዳዲስ መፍትሄ ለማቅረብ ነው፡፡
የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው አለሙ እንዳሉት “አነስተኛ ቢዝነሶች ለአገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ቢያደርጉም በተለይም በሴቶች የሚመሩ አነስተኛ የንግድ ተቋማት ከፍተኛ የፋይናንስ ፈተናዎች ይገጥሟቸዋል። ይህም የሆነበት ምክንያት በአብዛኛው በጥሬ ገንዘብ ላይ የተመሰረቱ ግብይቶች ላይ በመመስረትን የንግድ ሥራቸው በቂ ባልሆነና መደበኛ የፋይናንስ መዛግብት ሳይጠቀሙ በመስራታቸው እንዲሁም ሴቶች በንብረት ላይ የባለቤትነት መብት በማጣት የመያዣ መስፈርቶችን ካለማሟላት ጋር የሚያያዝ ነው።በዚህ አጋርነት እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ፣ የዳሸን ባንክን የአገልግሎት አቅም ለመገንባት፣ የብድር አቅርቦቶቻቸንን በማሻሻል የአነስተኛ የንግድ ባለቤቶችን ፍላጎት ለማሟላት እንዲሁም የተለያዩ ዲጂታል አገልግሎቶችንና ንግዶቻቸውን በተሳካ ሁኔታ ለማሳደግ የሚያስፈልጋቸውን ግብዓቶች እንዲያገኙ የሚያስችል የንድፈ ሃሳብ አገልግሎት ድጋፍ ለማድረግ የምንረባረብ ይሆናል፡፡
የዳሸን ባንክ ቺፍ ዲጂታል እና ኢንፎርሜሽን ኦፊሰር አቶ ዮሃንስ ሚሊዮን እንደተናገሩት፣ ዳሸን ባንክ ስድስተኛውን የስትራቴጂክ ዕቅድ ቀርፆ ወደ ስራ ሲያስገባ ከያዛቸው አበይት ተግባራት(Initiatives) አንዱ የኢኖቬሽን ልህቀት ማዕከል መገንባትና የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (Medium and Small Enterprises-MSME) አገልግሎቶችን የማቅረብ አቅም መጨመር ነው ብለዋል።በተጨማሪም ይህ የባንኩ እርምጃ የፋይናንስ አካታችነት እንዲሁም የፈጠራ አገልግሎት የታከለባቸውን የዲጂታል አገልግሎቶችን በማቅረብ ኢኮኖሚን መገንባትን የሚለውን አላማ ያደረገ ነው ብለዋል።
የጋራ ስምምነቱን መሰረት በማድረግ አክሲዮን፣ በተለይም ዳሸን ባንክ የአነስተኛ፣ መካከለኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችን ታሳቢ አድርጎ የሚያቀርባቸውን አዳዲስ አገልግሎቶች ሰው ሰራሽ አስተውህሎ (Artificial Intelligence-AI) በመጠቀም በተለይም በሴቶች ባለቤትነት የሚተዳደሩ ቢዝነሶች ምቹ የሆነ አዲስ የብድር አመዘጋገገብ ሞዴል እንዲኖራቸው ለማዘጋጀት ይረዳል፡፡ይህንን የተመዘገበ መረጃና ጥናትን መሰረት በማድረግ አዲስ የሚገነባው የኢኖቬሽን ልህቀት ማዕከል ቢዝነሶች ከብድር አቅራቢ ደንበኞቻቸው እንደ ብድር ያሉ መፍትሄዎችን ለማቅረብ፣ አካታች የቢዝነስ አገልግሎቶች፣ ፋይናንስ ነክ ያልሆኑ እንደ የቢዝነስ አስተዳደር ያሉ መፍትሄዎችን ለማገዝ የሚረዳ ይሆናል፡፡
ዳሸን ባንክ በዚህ ወቅት የኢኖቬሽን ልህቀት ማዕከሉን ዕውን ለማድረግ ጨረታ አውጥቶ፣ አስፈላጊውን የግንባታ ቅድመ ዝግጅት አጠናቋል።ይህ ፈር ቀዳጅ ግንባታ “ሁልጊዜ አንድ እርምጃ ቀዳሚ” ብሎ የተነሳውን ባንክ ቁርጠኝነት ከማሳየት ባሻገር በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ያለውን የቀዳሚነትና ፈርቀዳጅነት ሚና የሚያጠናክር ይሆናል።በቀጣይ ለባንኩ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች የኢኖቬሽን ወርክሾፕ የሚዘጋጅ ሲሆን፣ በተለይም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ጨምሮ ወቅቱ ያፈራቸው ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀምን በተመለከተ ከዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያው አብሮ ለመስራት ታቅዷል ብለዋል።
የአክሲዮን ምክትል ፕሬዚዳንት እና የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ አማካሪ የሆኑት ራሊያት ሱሞኑ አንዳሉት፣ “ኢትዮጵያ በአፍሪካ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ ኢኮኖሚዎች አንዷ ነች እና ትናንሽ ቢዝነሶች ደግሞ ይህንን እድገት በማስፋፋት ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።በዚህ ትብብር በፋይናንስ ኢኖቬሽን ውስጥ መሪ ከሆነው ከዳሸን ባንክ እና ሌሎች ስትራቴጂክ አጋሮች ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ውስጥ ለጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራዞች የበለጠ አካታች ሥነ-ምህዳር ለመገንባት የምናግዝ ይሆናል። በጋራ በመሆን በተለይም በሴቶች የሚመሩ ኢንተርፕራይዞችን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሌሎች የቴክኖሎጂ አማራጮችን በማቅረብ ተግባራዊ የምናደርግ ይሆናል።