Select Page

ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 25ኛ ዓመት በድምቀት አከበረ

በፕሮግራሙ ላይ ከባንኩ ጋር 25 አመት የሰሩ ሰራተኞች ፣ ደንበኞች፣ የቀድሞ የቦርድ አባላትና አመራሮች እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ በቀጣይ ወራት በባንክ ኢንዱስትሪው ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ፣ የደንበኞች ቀን፣ የባንኩን ታሪክ የሚዘክር የፎቶ አውደ ርእይ እና ወደ ዳሸን ተራራ የሚደረግ ጉብኝት የክብረ በአሉ መርሃ ግብሮች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ባንኩ እስከአሁን የሰነቀውን ልምድ በማጠናከር ለሚቀጥሉት አስር አመታት ባወጣው ፍኖተ ካርታና የአመስት አመት መራሔ እቅድ ከአፍሪካ ምርጥ ባንኮች መካከል አንዱ ለመሆን እየሰራ እንደሚገኝ አቶ አስፋው አመልክተዋል፡፡  በመክፈቻ ስነ-ስርአቱ ላይ የብሄራዊ ባንክ ገዥ አቶ ይናገር ደሴን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram