DubeAle | ዱቤ አለ!
ዱቤ የለም፣ ለዱቤ ነገ ይምጡ፣ ዱቤ አንሰጥም መባል በዳሸን ባንክ ቀርቷል!
እንዴት ካሉ ዱቤ አለ መልሱን ይዟል።
ዱቤ አለ ምንድን ነዉ?
ዱቤ አለ ዳሸን ባንክ ከኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ምርትና አገልግሎት የሚያቀርቡ የንግድ ድርጅቶች ጋር በጥምረት ያቀረበዉ በቴክኖሎጂ የታገዝ የዱቤ አሰራር ነው። ባንኩ ተለምዷዊውን ዱቤ በቴክኖሎጂ ከማዘመን በተጨማሪ በሸማቾች እና የንግድ ተቋማት መካከል መተማመን በመፍጠር ሸማቾች ፍላጎታቸውን በጊዜው እንዲሞሉ አምራቾችና እና አገልግሎት አቅራቢዎችም ሽያጫቸውን እንዲያሳድጉ ያግዛል።
እንዴት የዱቤ አለ ተጠቃሚ መሆን ይቻላል?
ከ18 ዓመት በላይ የሆነው ማንኛውም ሰው ዱቤ አለን መጠቀም ይችላል። በመጀመሪያ የዱቤ አለ መተግበሪያን ከጎግል ፕሌይ ወይም ከአፕ ስቶር ላይ ወደ ተንቀሳቃሽ ስልክዎ አዉርደዉ መመዝገብ ይችላሉ። በቀጠል ተቀጣሪ ከሆኑ ከሚሠሩበት መሥሪያ ቤት ስለ ሥራዎና ደመወዝዎ የሚገልጽ ደብዳቤ በማጻፍ ፤ በግል ስራ የሚተዳደሩ ከሆነ ደግሞ ንግድ ፈቃድ እና ሕጋዊ የገቢ ማስረጃዎን ይዘው በአቅራቢያዎ በሚገኝ የዳሸን ባንክ ቅርንጫፍ ለዱቤ አለ ማመልከት ይችላሉ። በዚያም በባለሙያ ታግዘው የደንበኝነት መረጃዎን ማሟላትና እና ከገቢ አቅምዎ ጋር የተገናዘበ የዱቤ ገደብዎን ማስወሰን ይችላሉ።
የዱቤ ገደብ
የዱቤ ገደብ (spending limit) ማለት በዱቤ ለመገበያየት የሚያስችልዎ በባንኩ የሚቀመጥልዎ የዱቤ ግብይት መጠን ነዉ፡፡ ለጊዜ የተፈቀደው የዱቤ ጣሪያ እስከ ብር 700,000 (ሰባት መቶ ሺህ ብር) ድረስ ያሻዎን መሸመት ይችላሉ፡፡ አስከተፈቀደልዎት የመገበያያ ጣሪያ ድረስ በአንድ ጊዜ ወይም በተለያየ ጊዜ እና የንግድ ተቋም ግብይት መፈጸም ይችላሉ። በዱቤ ገደቡ የሚፈልጉትን ምርትና አገልግሎት
ይሸምቱበታል እንጂ በጥሬ ገንዘብ መቀየር ወይም ወጪ ማድረግ አይቻልም፡፡
የዱቤ አለ ጥቅሞች
- በግዜያዊ አቅም ሳይወሰኑ ፍላጎትን ለማሳካት መቻል
ዛሬ ላይ የገንዘብ ውስንነት ቢኖርብዎትም አቅምዎን ባገናዘበ መልኩ ያሻዎትን በፈለጉት ጊዜ መሸመት መቻል። - ተመጣጣኝ ክፍያ
ተጠቃሚዎች የተራዘመ የመክፈያ ጊዜ ሲመቻችላችው ላገኙት እፎይታ የተማጣጠነ ክፍያ ይከፍላሉ። ክፍያውም በቁርጥ የሚታሰብ አነስተኛ መመዝገቢያና በተመቻቸው የተራዘመ ክፍያ ላይ የሚመሰረት የአገልግሎት ኮሚሽን ወይም ወለድ ይጨምራል። - ቀላል በተክኖሎጂ የታገዘ አሰራር
የዱቤ አለ መተግበሪያን በመጫን ለአገልግሎቱ መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን፣ መግዛት የሚፈልጓቸውን እቃዎች እና አገልግሎቶች ከነአቅራቢያቸው እና ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች ከዱቤ አለ መተግበሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ። - የገበያ ዕድል ያሰፋል
የባንኩ የዱቤ ሽያጭ ዋስትና የሸማቾችን ቁጥር የሚያሳድገው በመሆኑ የንግዱ ማህበረሰብ ተጨማሪ ገበያ ይፈጠርለታል። ይህም የሚሆነው ከዚህ በፊት ምርትና አገልግሎት ለመግዛት በአንድ ጊዜ መክፈል ይቸገሩ የነበረው የማህበረሰብ ክፍል አሁን በዱቤ አሰራር የመግዛት አቅም ስለሚፈጠርለት ነው። - የንግድ ተቋማትን ለማስተዋወቅ ያግዛል
የዱቤ አለ መተግበሪያ ላይ ምርትና አገልግሎቶቻቸውን የሚሸጡ አጋር ተቋማት የሚቀርቡ መሆኑ ጥሩ የመተዋወቂያ መንገድ ይፈጥራል።
የዱቤ አለ አግልግሎት ሰጪ ንግድ ማዕከላትን የት ማግኘት እችላለሁ?
የዱቤ አለ አገልግሎት ሰጪ የንግድ ማዕከላት ዝርዝር ዱቤ አለ መተግበሪያ ላይ ያለ ሲሆን ደንበኞች በተፈቀደላቸው የዱቤ መጠን መሰረት ጥሬ ገንዘብ ይዞ መሄድ ሳያስፈልጋቸው የዱቤ አለ መተግበሪያ ላይ የመረጡትን ምርትና አገልግሎት የንግድ ማዕከላቱ ጋር በአካል በመቅረብ በዱቤ መግዛት ይችላሉ፡፡
አከፋፈል
እንደ ተለምዷዊው የዱቤ አሰራር ሁሉ በዱቤ አለም ተጠቃሚዎች ዛሬ ለገዙት እቃና አገልግሎት ክፍያውን አዘግይተው የሚከፍሉ ሲሆን አከፋፈሉም እንደ ተጠቃሚው ምርጫ
ዱቤ አለን ከወለድ ነጻ መጠቀም ይቻላል?
የዱቤ አለ አገልግሎት ለሁሉ የማህበረሰባችን ክፍል የቀረበ ሲሆን ተጠቃሚዎች ዱቤ ያለወልድ የሚያገኙበት አሰራር ይበልጥ ይበረታታል።
የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን የዳሸን ባንክ ደንበኛ መሆን ያስፈልጋል?
የዱቤ አለ ተጠቃሚ ለመሆን የዳሸን ባንክ ደንበኛ መሆን ያስፈልጋል ይህም ብድሩ የሚከፈለው በባንኩ ካለ ሂሳብ መሆን ስላለበት ነው። የዳሸን ባንክ ደንበኛ ካልሆኑ ፈጥነው ባቅራቢያዎ ካለ ቅርንጫፋችን ሂሳብ ይክፈቱ እና የአገግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ።