“ዳሸን ሱፐር አፕ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ለመሆን ዕድል ይፈጥርልናል” አቶ ሚካኤል ለገሰ- የጎፈሬ ማርኬቲንግና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ

ዳሸን ሱፐር አፕ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ለመሆን ዕድል ይፈጥርልናል”
°አቶ ሚካኤል ለገሰ- የጎፈሬ ማርኬቲንግና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ
ዳሸን ባንክ በሱፐር አፕ አገልግሎቱ የተለያዩ ተቋማት ምርቶቻቸውን ለተጠቃሚዎች እንዲሸጡ ያቀረበው የመገበያያ አማራጭ (E-Commerce Platform) ዳሸን ሱፐር አፕን ከተቀላቀሉ ተቋማት አንዱ የሆነው ጎፈሬ በአጭር ጊዜ ውጤታማ እንዲሆን ዕድል የሚፈጥር መሆኑን የጎፈሬ ማርኬቲንግና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሚካኤል ለገሰ ገለፁ፡፡
“ዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ በስፖርት ኢንዱስትሪው ለሚሰሩ እንደ ጎፈሬ ላሉ ድርጅቶች ብቻ ሳይሆን የተለያዩ አገልግሎቶችን ለሚሰጡ ተቋማትም ትልቅ የምስራች ነው፡፡”
አቶ ሚካኤል ዳሸን ሱፐር አፕ ጎፈሬ ምርቶቹን የሚያቀርብበትን የሰራ ሂደት ከማቅለል በተጨማሪ የተጠቃሚዎችን ጊዜና ገንዘብ የሚቆጥብ በመሆኑ በየትኛውም አጋጣሚ አማራጩን ሕዝቡ እንዲጠቀመው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በ2010 ዓ.ም የተመሰረተው ጎፈሬ የስፖርት ትጥቆች አምራችና አቅራቢ ድርጅት በአገር ውስጥ፣ በምስራቅ አፍሪካ እንዲሁም በመላው ዓለም የስፖርት ትጥቅ ምርቶቹን ከሽያጭ ሱቆቹ በተጨማሪ በዳሸን ሱፐር አፕ በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡
ጎፈሬ ምንም እንኳን ዳሸን ሱፐር አፕን ከተቀላቀለ አጭር ጊዜ ቢሆነውም ከቀን ወደ ቀን በዚህ አማራጭ የሚጠቀሙ ደንበኞች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ ገልጸው ትእዛዝ እየተቀበሉ እንደሆነ አቶ ሚካኤል ተናግረዋል፡፡
ዳሸን ሱፐር አፕ ባቀረበው የመገበያያ አማራጭ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ተቋማት ገብተው ምርቶቻቸውን ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡
