Select Page

ዳሸን ባንክ ዳሸን አሜሪካን ኤክስፕረስ የተሰኘ አለምአቀፍ የዴቢት አገልግሎት ካርድ አስተዋወቀ

ዳሸን ባንክ ዳሸን አሜሪካን ኤክስፕረስ የተሰኘ አለምአቀፍ የዴቢት አገልግሎት ካርድ አስተዋወቀ

ዳሸን ባንክ ከአሜሪክን ኤክስፕረስ ጋር በመተባበር ዳሸን አሜሪካን ኤክስፕረስ የተሰኘ አለምአቀፍ የዴቢት አገልግሎት ካርድ በይፍ አቅርቧል፡፡ ይህ ካርድ ከኢትዮጵያ ዉጭ በተለያየ የአለም ክፍል ለንግድ ስራ የሚጓዙ ደንበኞች ግብይታቸዉን በዉጭ ምንዛሬ ለመፈፀም የሚያስችል በመሆኑ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋዉ አለሙ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ዳሸን ባንክ የዘርፉ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ዕድገትና የህግ ማሻሻያዎች የፈጠሩትን ዕድል በመጠቀም ጥራት ያለዉ አገልግሎት በመስጠትና ይህን መሰል የዘርፉን የፈጠራ ዉጤቶች በማቅረብ ሁሌም ቀዳሚ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ወደ ዉጭ ለሚጓዙ ኢትዮጵያዉያን በቀላሉ ክፍያ ለመፈፀም እንዲችሉ ዕድል የሚፈጥረዉን ይህን ካርድ በማስተዋወቁ ዳሸን ባንክ ደስተኛ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

ካርዱ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ከዚህ በፊት ጥሬ ገንዘብ ይዞ ወደ ዉጭ ከሚደረግ ጉዞ ጋር የተያያዙ ስጋቶችንም እንደሚያስቀር ገልፀዋል፡፡ ዳሸን ባንክ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዕዉቅና ካለዉ አሜሪካን ኤክስፕረስ ጋር በመሆን ካርዱን ማስተዋወቁ ትልቅ ዕምርታ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ደንበኞች ካርዱን በየትኛዉም የባንኩ ቅርንጫፍም ሆነ የዉጭ ምንዛሬ ቢሮ በማመልከት በአጭር ጊዜ ዉስጥ ማግኘት ይችላሉ፡፡

English Press Release

አማርኛ ጋዜጣዊ መግለጫ

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram