Select Page

ዳሸን ባንክ በአጋርነት ያዘጋጀው የሥዕል አወደ-ርዕይ ተካሄደ፡፡

ዳሸን ባንክ “ዳሸን ካልቸር ክለብ” “ከዋትስ አውት አዲስ ኢቨንትስ” ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የስዕልና ሌሎች የጥበብ ሥራዎችን ለሽያጭ የሚያቀርቡበት /Big Art Sale/አውደ-ርዕይ ለ19ኛ ጊዜ በሂልተን ሆቴል ተካሄዷል::

ለሁለት ቀናት የተካሄደው ይህ የጥበብ መድረክ ከ5,000 በላይ የጥበብ ወዳጆች ታድመውበታል፡፡

በሁነት ላይ ለሸያጭ የቀረቡት የስዕል ስራዎች ግብይትና የመግቢያ ትኬት ሽያጭ እንዲሁም ሌሎች የባንክ አገልግሎቶች በብቸኝነት በዳሸን ባንክ በኩል ተፈፅሟል፡፡

በአውደ ርዕዩ ላይ ከ250 በላይ የሥዕልና የጥበብ ተሰጥኦ ያላቸውን አዲስ ሥራዎቻቸው ለሽያጭ የቀርቡ ሲሆን፣ ለአዲስ ባለተሰጦኦዎች ዕድል ለመሠጠትና ከአንጋፋ ባለሙያዎች ጋር ለመተዋወቅ አጋጣሚውን ፈጥሯል።

በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ የስራና ክህሎት ሚንስትሯ ሙፈሪያት ካሚል የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

ከዚህ አውደ ርዕይ የተገኘው ገቢ ለበጎ አድራጎት ስራ ይውላል።

   

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram