Select Page

ዳሸን ባንክ ቱንስ ከተሰኘ ኩባንያ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ በቀላሉ ለመላክ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

ዳሸን ባንክ ቱንስ ከተሰኘ ኩባንያ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ በቀላሉ ለመላክ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

ዳሸን ባንክ ቱንስ ከተሰኘ ታዋቂ ዓለምአቀፍ የክፍያ ኔትወርክ ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት መስማማቱንና ይህም ደንበኞቹ ከተለያየ የዓለም ክፍል የሚላክላቸዉን ገንዘብ በቀላሉ ለመቀበል እንዲችሉ የሚያደርግ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ባንኩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠዉ መግለጫ ሁለቱ ተቋማት ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ በአጭር ጊዜና በተመጣጣኝ ክፍያ ለመላክ ይበልጥ በጋራ ለመስራት መስማማታቸዉን አመልክተዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ  ከዓለም አቀፍ የገንዘብ መላኪያ አማራጮች ይበልጥ ተዓማኒ ከሆነው ቱንስ ጋር በጋራ ለመስራት በመስማማቱ  ዳሸን ባንክ ደስተኛ ነዉ ብለዋል፡፡ ይህ የተለያዩ የቴክኖሎጂ  አማራጮችን ይበልጥ የሚያቀርብ ተቋም ደንበኞች በባንክ ሂሳባቸውም ሆነ በአሞሌ የሞባይል ዋሌት በኩል ከዉጭ የሚላክላቸዉን ገንዘብ ይበልጥ ፈጣንና አመቺ በሆነ መንገድ ለመቀበል እንደሚያስችላቸዉ ጠቁመዋል፡፡

ስምምነቱ የኢትዮጵያን የፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ ለመለወጥና ደንበኞቻችንን በተሻሉ የፈጠራ ዉጤቶች ለማገልገል በምናደርገው ጥረት ተጨማሪ አዉንታዊ እርምጃ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የቱንስ የአፍሪካ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት ሳንድራ ያኦ በበኩላቸዉ ከዳሸን ባንክ ጋር የተደረገዉ ስምምነት ደንበኞች ገንዘባቸዉን በቀጥታ በዳሸን ባንክ ሂሳባቸውና በአሞሌ ዋሌት ለመቀበልና ለመላክ የሚችሉበትን ዕድል እንደሚፈጥርላቸዉ አመልክተዋል፡፡

ከዳሸን ባንክ ጋር ከውጭ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ይበልጥ በጋራ ለመስራት እቅድ አለንም ብለዋል፡፡

አዳዲስ ደንበኞች በዳሸን ባንክ ሂሳብ በመክፈት በአሞሌ ዋሌት በኩል አገልግሎቱን በቀጥታ የማግኘት ፍላጎት ስለሚኖራቸዉ ዳሸን ባንክ የሚሰጠዉን የፋይናንስ አገልግሎት ይበልጥ እንደሚያሰፋው አስገንዝበዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ1995 የተቋቋመዉ ዳሸን ባንክ የተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮችን ለደንበኞቹ በማስተዋወቅ ፈር ቀዳጅ ነዉ፡፡ ባንኩ በመላዉ አገሪቱ በሚገኙ ከ460 በላይ ቅርንጫፎቹ መደበኛና ከወለድ ነፃ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ባንኩ በ2018 ያስተዋወቀዉ አሞሌ በአሁኑ ወቅት ከ3 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡

ቱንስ በአለም ላይ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎትን በማሳለጥ በጣም ታዋቂ ከሆኑ ተቋማት አንዱ ሲሆን በበርካታ ታዋቂ አለምአቀፍ ባንኮችና የገንዘብ ማስተላለፍ አገልጎሎት ተቋማትን በማገናኘት ገንዘብ ወደ ባንክ ሂሳብ፤ ሞባይል ዋሌትና ሌሎች አማራጮች ማስተላለፍ እንዲቻል ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ በሲንጋፖር  ዋና መስሪያ ቤቱ የሚገኘዉ ቱንስ በለንደን፤ ፓሪስ፤ ሻንጋይ፤ ኒዉ ዮርክ፤ ዱባይና ናይሮቢ ቅርንጫፎች አሉት፡፡

English Press Release

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram