Select Page
ዳሸን ባንክ ስፓንሰር ያደረገው ለባዊ ኢንተርናሽናል አካዳሚ “ፓን አፍሪካኒዝም” ባዛር ተካሄደ፡፡

ዳሸን ባንክ ስፓንሰር ያደረገው ለባዊ ኢንተርናሽናል አካዳሚ “ፓን አፍሪካኒዝም” ባዛር ተካሄደ፡፡

ዳሸን ባንክ ስፓንሰር ያደረገው ለባዊ ኢንተርናሽናል አካዳሚ “ፓን አፍሪካኒዝም” ባዛር ተካሄደ፡፡

የባዛሩ ብቸኛ የባንክ አጋር የነበረው ዳሸን ባንክ በባዛሩ ላይ የባንክ አገልግሎቶቹን ሰጥተዋል።

የለባዊ ኢንተርናሽናል አካዳሚ ስራ አስኪያጅ የሆኑት ፕሮፌሰር ፓኖስ ሃትዘያንድሪያስ ዳሸን ባንክ የባዛሩ ዋና አጋር በመሆኑ አመስግነዋል።

ዳሸን ባንክ ከዚህ ሁነት ባሻገር የለባዊ ኢንተርናሽናል አካዳሚ አጋር መሆኑን ያነሱት ስራ አስኪያጁ የትምህርት ቤቱ የፋይናንስ እንቅስቃሴ በዳሸን ባንክ በኩል እየተከናወነ ይገኛልም ብለዋል።

ለባዊ ኢንተርናሽናል አካዳሚ የዳሸን ባንክ ኮርፓሬት ደንበኛ መሆኑን የጠቆሙት ፕሮፌሰር ፓኖስ ባንኩ በተዘጋጀው ባዛር ላይ ከፍተኛ ድጋፍ በማድረጉ አካዳሚው ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

 

 

ዳሸን ባንክ በአጋርነት ያዘጋጀው የሥዕል አወደ-ርዕይ ተካሄደ፡፡

ዳሸን ባንክ በአጋርነት ያዘጋጀው የሥዕል አወደ-ርዕይ ተካሄደ፡፡

ዳሸን ባንክ በአጋርነት ያዘጋጀው የሥዕል አወደ-ርዕይ ተካሄደ፡፡

ዳሸን ባንክ “ዳሸን ካልቸር ክለብ” “ከዋትስ አውት አዲስ ኢቨንትስ” ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የስዕልና ሌሎች የጥበብ ሥራዎችን ለሽያጭ የሚያቀርቡበት /Big Art Sale/አውደ-ርዕይ ለ19ኛ ጊዜ በሂልተን ሆቴል ተካሄዷል::

ለሁለት ቀናት የተካሄደው ይህ የጥበብ መድረክ ከ5,000 በላይ የጥበብ ወዳጆች ታድመውበታል፡፡

በሁነት ላይ ለሸያጭ የቀረቡት የስዕል ስራዎች ግብይትና የመግቢያ ትኬት ሽያጭ እንዲሁም ሌሎች የባንክ አገልግሎቶች በብቸኝነት በዳሸን ባንክ በኩል ተፈፅሟል፡፡

በአውደ ርዕዩ ላይ ከ250 በላይ የሥዕልና የጥበብ ተሰጥኦ ያላቸውን አዲስ ሥራዎቻቸው ለሽያጭ የቀርቡ ሲሆን፣ ለአዲስ ባለተሰጦኦዎች ዕድል ለመሠጠትና ከአንጋፋ ባለሙያዎች ጋር ለመተዋወቅ አጋጣሚውን ፈጥሯል።

በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ የስራና ክህሎት ሚንስትሯ ሙፈሪያት ካሚል የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

ከዚህ አውደ ርዕይ የተገኘው ገቢ ለበጎ አድራጎት ስራ ይውላል።

   

 

ዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት “ሸሪክ“የጀመረበትን 6ተኛ አመት በድምቀት አከበረ

ዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት “ሸሪክ“የጀመረበትን 6ተኛ አመት በድምቀት አከበረ

ዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት “ሸሪክ“የጀመረበትን 6ተኛ አመት በድምቀት አከበረ

(አዲስ አበባ- የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም) ዳሸን ባንክ ሸሪክ የተሰኘ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የጀመረበትን 6ተኛ አመት ባከበረበት ዕለት ከደንበኞች በበጎ አደራጎት ፈንድ በአደራ የሰበሰበውን 12.5 ሚሊዮን ብር ለ18 አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጋፍ አደረገ፡፡

ዳሸን ባንክ በሚሰጠዉ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ብቻ አሁን ላይ ከ1 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን ማፍራት ችሏል፡፡ ይህንንም በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች አክብሯል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ለባንኩ አመኔታቸውን ለሰጡ ደንበኞች ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበው ወደፊትም ለላቀ ስኬት የሸሪዓህ መርህን በመከተል አዳዲስ የባንክ አገልግሎቶቸን እንደሚያቀርብ ገልፀዋል፡፡

አቶ አስፋው አክለውም በእለቱ በአደራ የተሰጣቸውን ገንዘብ የተረከቡ 18 አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅቶች የማህበረሰቡን ችግር ለመቅረፍ በሚያስችሉ ስራዎች ላይ እንዲያውሉት አደራ ብለዋል፡፡ በቀጣይም ባንኩ እነኚህንም ሆነ መሰል ሌሎች ተቋማት የማህበረሰቡን ችግሮች በዘላቂነት በሚፈቱ ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚሻ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዳሸን ባንክ የካቲት 26 ቀን 2010 ዓ.ም በአንድ መስኮት መስጠት የጀመረው አገልግሎት አድጎ ዛሬ ላይ ከ70 በላይ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በሚሰጡ ቅርንጫፎች እንዲሁም ከ800 በላይ በሆኑ ቅርንጫፎች ደግሞ በመስኮት ለደንበኞቹ የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ከደንበኞቹም ከ9.5 ቢሊየን ብር በላይ ማሰባሰብ የቻለ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ከ6 ቢሊየን ብር በላይ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ደንበኞቹ ፋይናንስ አድርጓል፡፡

ባንኩ ከወለድ-ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚጠይቀውን ሙያዊና ሸሪዓዊ ስነ-ምግባር ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህም ረገድ እ.ኤ.አ ህዳር 28 ቀን 2023 በባህሬን ማናማ በተካሄደው 9ኛው የኢስላሚክ ሪቴል ባንክ ሽልማት ላይ ጠንካራው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኢትዮጵያ የሚሰጥ ባንክ (The strongest Islamik Retail Banking Window in Ethiopia 2025) በሚል ተቀማጭነቱ ሎንዶን በሚገኘውና  በፋናንስ ዘርፍ ጥናትና ምርምር በሚሰራዉ  ኬምብሪጅ አይ ኤፍ ኤ(Cambridge IFA) የተሰኘ ተቋም ሽልማት አግኝቷል፡፡ ባንኩን ለዚህ ሽልማት ከአበቁት መሰፈርቶች አንዱ  ጠንካራ የሸሪዓህ አስተዳደር ማዕቀፍ በመተግበሩ ነው፡፡

ባንኩ በአለም አቀፍ ደረጃ የእስላማዊ ፋይናንስ ተቋማትን የሂሳብ፣ ኦዲት እና ሸሪዓህ መስፈርቶችን የሚያወጣው ተቋም (AAOIFI) ቋሚ አባል የሆነ በኢትዮጳያ ብቸኛው የፋይናንስ ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡

ሸሪክ የተለያዮ የተቀማጭ እና ኢንቨስትመንት አማራጮችን ይዞ የቀረበ ሲሆን ለአብነት ወዲዓህ(የአደራ ተቀማጭ ሂሳብ)፣ አን-ኒሰዕ ወዲአህ የሴቶች ሂሳብ፣ የሃጅ መንፈሳዊ ጉዞ ለማከናወን ደንበኞች ቁጠባ የሚያደርጉበት ሃጅ ወዲዓህ የቁጠባ ሂሳብ፣  በዉጭ ሃገር ምንዛሬ የሚከፈት ወዲዓህ የቁጠባ ሂሳብ፣ ቀርድ የተንቀሳቃሽ ሂሳብ (የቼክ ሂሳብ) እና የሙዳረባህ የጊዜ ገደብ ተቀማጭ(የኢንቨስትመንት ሂሳብ) ይገኙበታል፡፡

 

አዲሱ የዳሸን ባንክ ቦርድ አቶ ዱላ መኮንንን በድጋሚ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበር አድርጎ መረጠ

አዲሱ የዳሸን ባንክ ቦርድ አቶ ዱላ መኮንንን በድጋሚ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበር አድርጎ መረጠ

አዲሱ የዳሸን ባንክ ቦርድ አቶ ዱላ መኮንንን በድጋሚ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበር አድርጎ መረጠ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 08 ቀን 2016 ዓ.ም- የዳሸን ባንክ ባለአክሲዮኖች ባካሄዱት 30ኛው መደበኛ ጉባኤ የተመረጠውና የምርጫውም ውጤት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፀደቀለት አዲሱ የዳሸን ባንክ ቦርድ ባደረገው የመጀመሪያ ጉባኤ ላይ ባለፉት ሶስት ዓመታት ባንኩን በዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበርነት ያገለገሉትን አቶ ዱላ መኮንንን በድጋሚ በዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበርነት መርጧል፡፡

አዲሱ ቦርድ የካቲት 05፡ 2016 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ባካሄደው ጉባኤ ለቀጣይ ሶስት አመታት ዳሸን ባንክን በዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበርነት እንዲያገለግሉ በድጋሜ የመረጣቸው አቶ ዱላ መኮንን በአሁኑ ወቅት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማዕድን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

አዲሱ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ፣ እንዲሁም የማስተርስ ዲግሪያቸውንም በቢዝነስ አስተዳደር ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡ በአግሪካልቸራል ምህንድስናም ዲፕሎማ አላቸው፡፡

አቶ ዱላ በወንጂ ሸዋ፣ መተሃራ እና ፊንጫ ስኳር ፋብሪካዎች እንዲሁም በሌሎች ተቋማት በአጠቃላይ ለ24 አመታት አገልግለዋል፡፡ በሊሙ ቡና ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የሰሩት አቶ ዱላ ከዚያ በኋላም የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅም ነበሩ፡፡ የኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ ኃ/የተወ/የግል/ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ዱላ በሆራይዘን ፕላንቴሽን ኃ/የተወ/የግል/ኩባንያም በከፍተኛ ኃላፊነት ሰርተዋል፡፡

አዲስ የተመረጡት የቦርድ አባላት እና ባንኩን ላለፉት ሶስት ዓመታት ያገለገሉት የቦርድ አባላት የስራ ርክክብ ያደረጉ ሲሆን ንዑስ ኮሚቴዎችንም አዋቅረዋል፡፡ ባንኩ አዲስ ለተመረጡት የቦርድ አባላት አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴውን አስመልክቶ ገለፃ ሰጥቷል፡፡

ዳሸን ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የአየር ትራንስፖርት ክፍያ አገልግሎት ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የአየር ትራንስፖርት ክፍያ አገልግሎት ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የአየር ትራንስፖርት ክፍያ አገልግሎት ይፋ አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ዳሸን ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞች የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቅመው ክፍያውን ቆይተው የሚከፍሉበትን አዲስ የክፍያ አማራጭ በጋራ አስተዋወቁ።

አቶ ዮሃንስ ሚሊዮን የዳሽን ባንክ ዲጂታል ባንኪንግ ዋና መኮንን:‘ጉዞዎ ይቀድማል ክፍያው ይደርሳል’ በሚል የተሰየመው ይህ አገልግሎት በደንበኞች ምርጫ መሰረት በ6 ወር ወይም በ12 ወር የብድር ክፍያ የሚሰጥ መሆኑን አመልክተዋል። ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን በዳሸን ባንክ የሂሳብ ቁጥር መክፈት እንደሚገባቸው እና በተጨማሪም በባንኩ ቢያንስ ለሶስት ወራት አገልግሎት ያገኙ መሆን እንደሚኖርባቸውም ጠቁመዋል።  

አቶ ዮሃንስ አክለውም አገልግሎቱን ለማግኘት ደንበኞች አቅራቢያቸው ወደሚገኝ የዳሸን ባንክ ቅርንጫፍ በሚያመሩበት ወቅት አስፈላጊ ሰነዶችን ማሟላት የሚገባቸው ሲሆን ማስያዣም ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸውም ገልፀዋል።

ስምምነቱን አስመልክቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና የንግድ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ያዴቻ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል፣ “የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኛ ተኮር አሰራርን እንደመከተሉ የተለያዩ ዘመናዊ እና ለመጠቀም ቀላል የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን እያስተዋወቀ ይገኛል። የምናበለጽጋቸው ቴክኖሎጂዎች ለደንበኞቻችን ምቹ መሆናቸው እንደተጠበቁ ሆኖ የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት ጋርም የተጣጣሙ እንዲሆኑ እናደርጋለን። ዛሬም አጋራችን ከሆነው የዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር ለደንበኞቻችን ያቀረብነው አዲስ የክፍያ አማራጭ ተግባራዊ እንዲሆን የሞባይል መተግበሪያችን ከአዲሱ የክፍያ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ እንዲሆን አድርገናል። በዚሁም መሰረት ደንበኞች ስለክፍያ ሳይጨነቁ ጉዟቸውን ማቀድ የሚጀምሩበትን ‘Fly Now Pay Later’ ተብሎ የተሰየመውን የክፍያ አማራጭ ተግባራዊ ማድረጋችንን ስንገልጽ በደስታ ነው። ይህ የድህረ-ጉዞ ክፍያ አማራጭ ፕሮጀክት ዕውን እንዲሆን ከአየር መንገዳችን እና ከዳሽን ባንክ በኩል ለተሳተፉ አካላት ያለኝን ምስጋና በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እፈልጋለሁ።”

አዲሱን አገልግሎት ለመጠቀም አንድ ደንበኛ አስፈላጊ ቅድመ-ሁኔታዎችን ካሟላ በኋላ በቅርንጫፉ የተፈቀደለትን የብድር መጠን የሚወስድ ሲሆን የተፈቀደለትን ገንዘብ ለመጠቀም የሚያስችል የአንድ ጊዜ መለያ ቁጥር መልዕክትም በተንቀሳቃሽ ስልኩ የሚደርሰው ይሆናል። በመቀጠልም ደንበኛው የተሰጠውን መለያ ቁጥር በአየር መንገዱ የሞባይል መተግበሪያ ላይ በማስገባት ትኬት መቁረጥና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላል።

ደንበኞች የተፈቀደላቸው የብድር መጠን ሲያልቅ ማደስ የሚችሉ ሲሆን በአንዴ የወሰዱትን ብድርም ለተለያዩ በረራዎች ከፍለው መጠቀም ይችላሉ።

አገልግሎቱ በተለይም በንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ፣ ጅምላ አስመጪዎች እና ለዕረፍት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ውጭ ለሚሄዱ ደንበኞች አመቺ ነው።

በሁለቱ ተቋማት ስምምነት በቀረበው በዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈቀደው የብድር ገንዘብ መጠን እስከ ስድስት መቶ ሺህ (600,000) ብር የሚደርስ ነው።

የሚፈቀደው ብድር ወለድ የሚታሰብበት ሲሆን ይህም ደንበኛው በመረጠውና ብድሩን በወሰደበት የጊዜ ገደብ ከብድሩ ጋር አብሮ የሚከፈል ነው።

ብሔራዊ አየር መንገዱ እና ዳሽን ባንክ ወደፊትም የደንበኞችን አገልግሎት ለማዘመን አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም በትብብር መስራታቸውን ይቀጥላሉ።

Ethiopian, Dashen Bank Launch ’Fly Now Pay Later’ Service Package

Ethiopian, Dashen Bank Launch ’Fly Now Pay Later’ Service Package

Ethiopian, Dashen Bank Launch ’Fly Now Pay Later’ Service Package

  • The service allows passengers to fly without paying upfront
  • Ethiopian integrated the new Dashen Credit service to its Mobile app

December 28, 2023, Addis Ababa

Dashen Bank and the Ethiopian Airlines Group have jointly launched an innovative service package dubbed ‘Fly Now Pay Later’. This new technological innovation offers unprecedented flexibility and convenience for travelers allowing them to experience the unique opportunity to fly first and make payment at a later date. This pioneering move will redefine the travel experience.

The impact of technology in the travel industry is not only limited to registering business growth and profitability, but more importantly, it enhances the travel experience by reducing unnecessary steps that have traditionally contributed to travel ordeals.

Expressing his delight about the newly introduced service, Mr. Yohannes Million, Chief Digital Banking Officer of Dashen Bank said, “Fly Now Pay Later (FNPL) is an innovative way to purchase flights that allows travellers to book their trips without paying the full price upfront. The service will be available based on the customers’ choice of a 12- or 6-month payment period. Additionally, customers must open a bank account at Dashen Bank and remain as customers for at least three months in order to enjoy this service.”

Mr. Yohannes also emphasized that when customers go to the nearby Dashen Bank branch to apply, they are expected to present the necessary documents along with a guarantee.

Lauding the fruitful joint effort by the Ethiopian and Dashen team, Mr. Lemma Yadecha, Group Chief Commercial Officer of Ethiopian Airlines, said, “At Ethiopian, we place great value on system and technology modernization. System is one of our strategic growth pillars, and we continue to invest heavily in introducing cutting-edge technologies as part of our customer-centric endeavors. The new payment service we are launching today, ‘Fly Now, Pay Later,‘ will offer customers additional payment flexibility and enhance the customer experience. We have integrated our mobile app with the new payment strategy provided by Dashen Bank. We will further strive to make our system compatible with the best practices of other domestic banks as well.”

The credit period for this service is set for six to twelve months, and the credit limit can be renewed at the end of the credit tenure. Dashen Bank’s IT department has developed a desktop application that is integrated with the Ethiopian Airlines’ FlyGate application. Ethiopian Airlines, through its booking system, will provide confirmed passenger flight bookings and services upon successful payment confirmation received from Dashen Bank through FlyGate.

To use this service, customers will receive a spending limit from the Dashen Bank branch and an SMS confirmation that should be entered into Ethiopian Mobile app to purchase flight tickets. Passenger flight tickets can be purchased once or multiple times, up to the facility limit.

The credit limit is determined based on the customers’ borrowing capacity, up to a maximum of 600 thousand birr. The Fly Now Pay Later payment strategy has increasingly gained popularity in the travel industry.

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram