Select Page

ዳሸን ባንክ፣ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደርና የከተማው የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ

ዳሸን ባንክ፣ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደርና የአርባ ምንጭ ከተማ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በጋራ ለመስራት የሚያስችል የሶስትዮሽ የጋራ ስምምነት ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ ሃይሌ ሪዞርት ተፈራርመዋል፡፡

በዚህ ስምምነት መሰረት ዳሸን ባንክ በአርባ ምንጭ ከተማና አካባቢው የተለያዩ የባንክ አገልግሎት አማራጮችን በስፋት እንዲያቀርብና በጋሞ ዞን አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ያደርጋል፡፡

ዳሸን ባንክ በከተማውና አካባቢው አገልግሎቱን ተደራሽና ለማድረግና አዳዲስ ቅርንጫፎችን ለመክፈት በሚያደርገው ጥረት የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ በስምምነቱ ተመልክቷል፡፡

ከአርባ ምንጭ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበርም ህብረት ስራ ማህበራት፣ የንግድ ማህበራትና ሌሎች መሰል መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ከባንኩ ጋር ይበልጥ ተሳስረው የሚሰሩባቸው የተለያዩ አማራጮች በስምምነቱ ተወስተዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አርባምንጭ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጋሞ ዞንና የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ የጋሞ አባቶች እንዲሁም የአርባምንጭ ከተማ ንግድ ማህበራት ዘርፍ ምክር ቤት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገዉላቸዋል።

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram