Select Page

ዳሸን ባንክ በደገፈው የዘንድሮው የሶልቭ ኢት ሀገር ዓቀፍ የፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች የስራ ማስጀመሪያ የገንዘብ ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡

አይኮግ ኤኒዋን ካን ኮድ ኮንሰልታንትስ ኃ.የተ.የግ.ማ፣ ከአሜሪካን ኤምባሲ እና ከዳሽን ባንክ አ.ማ፣ እንዲሁም እንደ ዋንኛ ባለድርሻ አካል ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የትምህርት ሚኒስቴር ጋራ በመተባበር በተተገበረዉ የዘንድሮው የሶልቭ ኢት 2023 የፈጠራ ውድድር ከተመዝገቡ ከ2000 በላይ ተሳታፊዎች መካከል የከተማ ዓቀፍ (City Hub) ዉድድሩን አሸንፈዉ ለመጨረሻዉ ዙር የቡትካምፕ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዉድድር ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች ከዳሸን ባንክ የስራ ማስጀመሪያ የገንዘብ ሽልማት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዳሸን ባንክ አጋርነት የተተገበረዉ የሶልቭ ኢት 2023 ሀገር አቀፍ ውድድር በኢትዮጲያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚግኙ ባለተስዕጦ ወጣቶች የየአካባቢያቸዉን ማህበረሰብ ችግር በመረዳት ፈጠራን እና ቴክኖሎጂን ያማከለ መፍትሄ የሚሆን የንግድ ሃሳብ፣ ምርት ወይንም አገልግሎት በማቅረብ የሚወዳደሩበት እና ወደ ስራ እንዲገቡ የተለያዩ የድጋፍ ስርዓቶችን የሚያመቻች እንዲሁም የሰራ ፈጣሪነት አስተሳሰብን ማሳደግ ያለመ ሲሆን፣ በስድስት ከተሞች ማለትም በባህር ዳር፣ ደሴ፣ ጅማ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ድሬዳዋ እና አዲስ  አበባ ተካሂዷል፡፡ በዚህም በርካታ ዩኒቨርሲቲዎችን፣ኮሌጆችን፣ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ተማሪዎችን በማሳተፍ የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ ጭምር ዕድል ፈጥሯል፡፡

አይኮግ ኤኔዋን ካን ኮድ በተሰኘዉ ድርጅት አማካኝነት የሚዘጋጀው የሶልቭ ኢት ሀገር አቀፍ የፈጠራ ውድድር ከ18-28 ዓመት ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች በቴክኔሎጂ ዘርፍ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን እንዲያቀርቡ እና ወደ ስራ እንዲገቡ ዕድል በመፍጠር የማህበረሰቡን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በመፍታት ላይ ያተኮረ ፕሮጀክት ነው፡፡

አይኮግ ኤኔዋን ካን ኮድ፣ በሶልቭ ኢት ውድድር በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያለዉን የፈጠራ ሥራ ጅምሮችን በመደገፍ እና በማበረታት በዘርፍ የተሰማሩ ስራ ጀማሪ ወጣቶች የሚፈልጉትን ድጋፍ ማለትም የንግድ ሥራ ፈጠራ ስልጠናዎች፣ የገንዘብ ድጋፍ፣ የኢንቨስትመንት ትሥሥር በመፍጠር እና ቡት ካምፕ በማዘጋጀት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል።

በዘንድሮው ውድድርም የቀረቡት የፈጠራ ስራዎች በትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና እና ሌሎች ዘርፎች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ያለሙ ጅምር ስራዎች ናቸው፡፡ ከስድስቱ የኢትዮጲያ አካባቢዎች የተዉጣጡት የመጨረሻዉ ዙር ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ በቡትካምፕ ቆይታ የ አንድ ሳምንት ዝግጅት ያደረጉ ሲሆን፥ የውድድሩ አሸናፊዎች ባቀረቡት የፈጠራ ስራ ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችል የስራ ማስጀመሪያ መነሻ ገንዘብ ድጋፍ በዳሸን ባንክ ተበርክቶላቸዋል፡፡በዉድድሩ መስፈርት እና በዳኞቸ ዉጤት መሰረት የዉድድሩ አሸናፊዎች በድምሩ የ1 ሚሊዮን ብር የስራ ማስጀመሪያ አግኝተዋል።

 

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram