ስለ ሰላም ባዛርና ኤግዚቢሽን በይፋ ተከፈተ
ስለ ሰላም ባዛርና ኤግዚቢሽን በይፋ ተከፈተ
ዳሸን ባንክ በዛሬው ዕለት በይፋ በተከፈተው ” ስለ ሰላም ባዛርና ኤግዚቢሽን” ላይ አዳዲስ አገልግሎቶቹን እያስተዋወቀ ይገኛል።
ባንኩ “ሾፐርስ እና ትራቭለርስ ክለብ ካርድ” ፣ “አሁን ይብረሩ ቀስ ብለው ይክፈሉ” (Fly now Pay Later) ፣ “ከወለድ ነጻ ዱቤ አለ” እንዲሁም ሌሎች ከዚህ ቀደም የተዋወቁና አዳዲስና ዘመናዊ አገልግሎቶችን እያስተዋወቀ ይገኛል።
በተጨማሪም ባንኩ ሙሉ የባንክ አገልግሎቶችን በባዛርና ኤግዚቢሽኑ ላይ እየሰጠ ይገኛል።