Select Page
ዳሸን ባንክ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት  ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ

ዳሸን ባንክ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ

ዳሸን ባንክ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ

ዳሸን ባንክ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ድጋፍ እንዲውል የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበርክቷል።
 
የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና ቺፍ ባንኪንግ ኦፕሬሽንስ ኦፊሰር አቶ ጥበቡ ሰለሞን ዳሸን ባንክ በዞኑ ነዋሪዎች ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን በድጋሚ ገልፀው ባንኩ የአካባቢውን ነዋሪዎች ለመርዳት በሚደረገው አገራዊ ጥረት የበኩሉን ድጋፍ ለማቅረብ ስፍራው ድረስ መገኘቱን አመልክተዋል።
 
ዳሸን ባንክ ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረትም የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ አቶ ጥበቡ ገልጸዋል።
 
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ አጌና ድጋፉን ይዘው በስፍራው ለተገኙ የዳሸን ባንክ ከፍተኛ አመራሮች አደጋው ስላደረሰው ጉዳት ገለፃ ከሰጡ በኋላ ዳሸን ባንክ በአካባቢው ከሚገኘው ቅርንጫፍ ጀምሮ ላበረከተው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
 
ከዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና ቺፍ ባንኪንግ ኦፕሬሽንስ ኦፊሰር አቶ ጥበቡ ሰለሞን በተጨማሪ የባንኩ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ ኤልያስ ሁሴን፣ የዳሸን ባንክ ማርኬቲንግ እና ብራንዲንግ ዳይሬክተር አቶ እንዳለ ገብረስላሴ፣ የባንኩ የወላይታ ቀጠና ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ ታዲዮስ ተስፋዬ እና የባንኩ የአርባምንጭ አካባቢ ስራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል አለማየሁ ተገኝተው ድጋፉን አበርክተዋል።
 
VISA, Mastercard and Amex card holders can now donate to Ethiopian Red Cross Society online

VISA, Mastercard and Amex card holders can now donate to Ethiopian Red Cross Society online

VISA, Mastercard and Amex card holders can now donate to Ethiopian Red Cross Society online

ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 25ኛ ዓመት በድምቀት አከበረ

ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 25ኛ ዓመት በድምቀት አከበረ

ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 25ኛ ዓመት በድምቀት አከበረ

በፕሮግራሙ ላይ ከባንኩ ጋር 25 አመት የሰሩ ሰራተኞች ፣ ደንበኞች፣ የቀድሞ የቦርድ አባላትና አመራሮች እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ በቀጣይ ወራት በባንክ ኢንዱስትሪው ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ፣ የደንበኞች ቀን፣ የባንኩን ታሪክ የሚዘክር የፎቶ አውደ ርእይ እና ወደ ዳሸን ተራራ የሚደረግ ጉብኝት የክብረ በአሉ መርሃ ግብሮች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ባንኩ እስከአሁን የሰነቀውን ልምድ በማጠናከር ለሚቀጥሉት አስር አመታት ባወጣው ፍኖተ ካርታና የአመስት አመት መራሔ እቅድ ከአፍሪካ ምርጥ ባንኮች መካከል አንዱ ለመሆን እየሰራ እንደሚገኝ አቶ አስፋው አመልክተዋል፡፡  በመክፈቻ ስነ-ስርአቱ ላይ የብሄራዊ ባንክ ገዥ አቶ ይናገር ደሴን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ዳሽን ባንክ ኤስ ኤን ቪ ኔዘርላንድስ ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር 240 ሺህ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

ዳሽን ባንክ ኤስ ኤን ቪ ኔዘርላንድስ ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር 240 ሺህ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

ዳሽን ባንክ ኤስ ኤን ቪ ኔዘርላንድስ ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር 240 ሺህ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

ዳሽን ባንክ ኤስ ኤን ቪ ኔዘርላንድስ ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር 240 ሺህ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

መርሃ ግብሩ በአማራ እና በትግራይ ክልል የሚገኙ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ ወጣቶችን ለመደገፍ ያለመ ነው ፡፡

ለአምስት አመታት በሚተገበረው በዚህ መርሃ ግብር ዳሽን ባንክ የወጣቶቹን የቁጠባ ባህል ለማዳበር ፤ የገቢ አያያዝ ባህል ለማጎልበት የሚያስችሉ እና ሌሎች ተያያዥ ድጋፎችን ያደርጋል፡፡

ዳሸን ባንክ ለገበታ ለሃገር ፕሮጅክቶች ማስፈጸሚያ የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ዳሸን ባንክ ለገበታ ለሃገር ፕሮጅክቶች ማስፈጸሚያ የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ዳሸን ባንክ ለገበታ ለሃገር ፕሮጅክቶች ማስፈጸሚያ የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ዳሸን ባንክ ገበታ ለሀገር በሚል ስያሜ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲተገበሩ በመንግስት ለታቀዱ ግዙፍ የልማት ፕሮጅክቶች ማስፈጸሚያ ይሆን ዘንድ የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
በያዝነው ዓመት “ገበታ ለሃገር’’ በሚል ጎርጎራ፣ወንጪና ኮይሻን የማስዋብ ፕሮጀክቶች እንደተጀመሩ ይታወቃል። ለሦስቱ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ቢያንስ ስድስት ቢሊዮን ብር ያህል እንደሚያሰፈልግም በመንግሥት ተነግሯል፡፡ ዳሸን ባንክም ለነዚህ ለሶስቱ ፕሮክቶች ለእያንዳንዳቸዉ 10 ሚሊየን ብር በአጠቃላይ 30 ሚሊየን ብር እንደሚለግስ ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ተናግረዋል፡፡

ዳሸን ባንክ ለተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር 3 ሚሊየን ብር አበረከተ

ዳሸን ባንክ ለተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር 3 ሚሊየን ብር አበረከተ

ዳሸን ባንክ ለተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር 3 ሚሊየን ብር አበረከተ

ባንኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “አዲሱን አመት በአዲስ ተስፋ ብርሃን” በሚል መሪ ቃል ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ በከተማው የሚገኙ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን ለማገዝ ድጋፉን አበርክቷል፡፡
ዳሸን ባንክ ባለፈው አመት ለዚሁ መርሃ ግብር 1 ሚሊዮን አንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር ማበርከቱ ይታወሳል፡፡ ባንኩ ባለፈው በጀት አመት በአጠቃላይ 170 ሚሊየን ብር ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች አውሏል ፡፡

Facebook
Twitter
YouTube
LinkedIn
Instagram
Telegram